የአንተን ፡ ሰላም ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ አውርድልን (Yanten Selam Oh Eyesus Awerdelen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የአንተን ፡ ሰላም ፡ ኦ! ኢየሱስ ፡ አውርድልን
በሁከት ፡ የሚያድል ፡ ጸጥታን
በእንግድነት ፣ ተስፋን ፡ የሚሰጠን
ለገነት ፡ የሚለውጥ ፡ በረሃን

በአጭር ፡ ጊዜ ፣ ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ መታገል
አይዞህ ፡ ልጄ! ብለህ ፡ ስትመክረኝ
በአጭር ፡ ጊዜ ፣ መዝራትና ፡ ማገልገል
ቀኑ ፡ ለመከር ፡ እስኪነጋልኝ

በአጭር ፡ ጊዜ ፣ ይገኛል ፡ ሥቃይ ፡ ሃዘን
ነፍሣችን ፡ በዚህ ፡ ዘወትር ፡ ይጸማል
ወዲያ ፡ ግን ፣ ደስታና ፡ ትርፍ ፡ ሊቆየን
ከሕይወት ፡ ወንዝ ፣ ነፍሣችን ፡ ይረካል

በአጭር ፡ ጊዜ ፣ አንተ ፡ እስክትመጣ
መብራቴን ፡ አብርቼ ፡ ልጠብቅህ
ስትመጣ ፡ ሊሆነኝ ፡ ደስታ ፡ ዕልልታ
ሁልጊዜ ፣ ስብሓት ፡ ይሁንልን