ያን ፡ ክቡር ፡ ዕንቁ ፡ አገኘሁኝ (Yan Kibur Enqu Agegnehugne)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ያን ፡ ክቡር ፡ ዕንቁ ፡ አገኘሁኝ
እርሱም ፡ መድኃኒቴ
አገኘው ፡ ዘንድ ፡ ተመኘሁኝ
አሁንም ፡ ነው ፡ ሃብቴ

ተነሽ ፡ ኦ! ነፍሴ ፡ ዘምሪ
ደስታሽንም ፡ ግለጭ
ንጉሥሽንም ፡ አክብሪ
ለርሱም ፡ ምሥጋና ፡ ስጭ

ከአምላክ ፡ ጋር ፡ አስታረቀኝ
የዕውነቱንም ፡ ቃል
በመንፈሱ ፡ አስታወቀኝ
በልቤም ፡ ነግሧል

የጌቶች ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነው
የእኔም ፡ እረኛ ፡ ነው
ቀንበሩንም ፡ ስሸከመው
በዕውነት ፡ መልካም ፡ ነው

ድህ ፡ ብሆንም ፡ ምስኪንም
ብርታቴ ፡ እርሱ ፡ ነው
በኃጢአት ፡ ስጨነቅም
የኃጢአት ፡ ማስተሰረይ ፡ ነው

እርሱ ፡ ነው ፡ ጽድቄ ፡ ሕይወቴም
ሰላሜም ፡ ጤናዬም
እርሱ ፡ ነው ፡ ደኅንነቴም
ድፍረቴም ፡ ተስፋዬም

ዕዳዬን ፡ የደመሰስኸው
ኦ! ርኅሩኅ ፡ መድኅኔ
አንተ ፡ ሁሉ ፡ በሁሉው
ዘወትር ፡ ሁን ፡ ለእኔ