የአምላኬን ፡ ውለታ ፡ ሁሉ (Yamlakien Wuleta Hulu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የአምላኬን ፡ ውለታ ፡ ሁሉ
ልቆጥረው ፡ ያቅተኛል
ከላይ ፡ እንደወረደው ፡ ጠሉ
በሁሉ ፡ ተረፍርፏል
የአምላኬን ፡ ውለታ ፡ ሁሉ
ልቆጥረው ፡ ያቅተኛል

ሳይሰየም ፡ ሳይመዘን ፡ ይቀራል
የፍቅሩ ፡ የፀጋውም ፡ ብዛት
በጨለማ ፡ ውስጥ ፡ ግን ፡ ያበራል
በሌትም ፡ ይሰጣል ፡ ንጋት
ሳይሰየም ፡ ሳይመዘን ፡ ይቀራል
የፍቅሩ ፡ የፀጋውም ፡ ብዛት

ልመዝነው ፡ ከቶ ፡ ባይቻለኝ
ይልቅ ፡ ላመሰግነው ፡ ነኝ
የውለታው ፡ ትሩፋት ፡ ካለኝ
የፍቅሩ ፡ ብርታት ፡ ታወቀኝ
ልመዝነው ፡ ከቶ ፡ ባይቻለኝ
ይልቅ ፡ ላመሰግነው ፡ ነኝ