የአምላክ ፡ ዋጋው ፡ ምሥጋና ፡ ነው (Yamlak Wagaw Mesgana New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝየአምላክ ፡ ዋጋው ፡ ምሥጋና ፡ ነው (፪x)
ጨለማን ፡ ሌሊት ፡ ብርሃን ፡ ሲያደርገው
ተራራን ፡ ንዶ ፡ ሲያደላድለው
ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የምንከፍለው?

ምድር ፡ ሞላዋ ፡ ሁሉ ፡ የእርሱ
ሰማየ ፡ ሰማያት ፡ ባሕር ፡ የብሱ
እርሱን ፡ የሚያረካው ፡ ምን ፡ አለንና?
ሌላ ፡ ከአፋችን ፡ ምሥጋና

አዝየአምላክ ፡ ዋጋው ፡ ምሥጋና ፡ ነው (፪x)
ጨለማን ፡ ሌሊት ፡ ብርሃን ፡ ሲያደርገው
ተራራን ፡ ንዶ ፡ ሲያደላድለው
ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የምንከፍለው?

የሞተን ፡ ተስፋ ፡ ኃይሉን ፡ ሲያድስ
የምርኮን ፡ አጥር ፡ ሲያፈራርስ
ሕዝቡን ፡ በእሣት ፡ ሲያሻግረው
ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የምንከፍለው?

አዝየአምላክ ፡ ዋጋው ፡ ምሥጋና ፡ ነው (፪x)
ጨለማን ፡ ሌሊት ፡ ብርሃን ፡ ሲያደርገው
ተራራን ፡ ንዶ ፡ ሲያደላድለው
ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የምንከፍለው?

የእንባውን ፡ ፍሬ ፡ ጠላት ፡ ሲያየው
ዘሩን ፡ በደስታ ፡ ሲሸከመው
ጠላት ፡ ከማዶ ፡ ሆዱ ፡ ሲደብን
የጌታ ፡ ዋጋው ፡ ተመስገን

አዝየአምላክ ፡ ዋጋው ፡ ምሥጋና ፡ ነው (፪x)
ጨለማን ፡ ሌሊት ፡ ብርሃን ፡ ሲያደርገው
ተራራን ፡ ንዶ ፡ ሲያደላድለው
ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የምንከፍለው?

የዋይታን ፡ ሌሊት ፡ ሲያነጋጋው
ልቅሶን ፡ በደስታ ፡ ሲለውጠው
የዛለውን ፡ ልብ ፡ ሲያበረታው
ጌታ ፡ ተመስገን ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝየአምላክ ፡ ዋጋው ፡ ምሥጋና ፡ ነው (፪x)
ጨለማን ፡ ሌሊት ፡ ብርሃን ፡ ሲያደርገው
ተራራን ፡ ንዶ ፡ ሲያደላድለው
ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የምንከፍለው?