የአምላክ ፡ በግ ፡ በመስቀል ፡ ላይ (Yamlak Beg Bemesqel Lay)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የአምላክ ፡ በግ ፡ በመስቀል ፡ ላይ
የተቀበለውን ፡ ሥቃይ
በዕምነት ፡ ስመለከተው
ሕይወትና ፡ ጤና ፡ ነው

ያን ፡ ጊዜ ፡ የፈሰሰም
ቅዱሱ ፡ የልጁ ፡ ደም
በአምላክ ፡ ፍርድ ፡ አጸደቀኝ
ከክፋቴም ፡ አጠበኝ

ወንበዴውም ፡ የጸለየው ጸሎት
ልመናዬም ፡ ነው
አስበኝ ፡ በመንግሥትህ ፡ ስል
የፀጋ ፡ መልስ ፡ ሰጠህ

ኢየሱስ ፡ ከአምላክ ፡ ተጥለህ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ ተሰቅለህ
እኔ ፡ ከአምላክ ፡ እንዳልጣል
ፍፁም ፡ ተስፋ ፡ ሰጥተሃል

ዓብ ፡ አሁን ፡ ነው ፡ አባቴ
እኔም ፡ በመድኃኒቴ
የሚወደኝ ፡ ልጁ ፡ ነኝ
በዕቅፉም ፡ ውስጥ ፡ ተቀበለኝ