ያለ ፡ ደስታ ፡ ስኖር (Yale Desta Senor)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ያለ ፡ ደስታ ፡ ስኖር ፡ ሳለሁ
ክቡር ፡ ደምህ ፡ ፈሰሰልኝ
ምሕረትህን ፡ ላገኝ ፡ መጣሁ
የአምላክ ፡ በግ ፡ መጣሁ ፡ እርዳኝ
ከጨለማ ፡ ልዳን ፡ ብዬ
ሳልዘጋጅ ፡ ለጌታዬ
ጊዜያቱ ፡ አለፈብኝ
የአምላክ ፡ በግ ፡ ና ፡ ውሰደኝ
በምድር ፡ ተንገላትቼ
በችግርና ፡ በጭንቀት
እንደዚህ ፡ ኖርሁ ፡ ተዋግቼ
ና ፡ ና ፡ አድነኝ ፡ ከጭንቀት
መጣሁ ፡ ትቀበለኛለህ
ይቅርታን ፡ ትሰጠኛለህ
የአንተን ፡ ተስፋ ፡ አምነዋለሁ
የአምላክ ፡ በግ ፡ መጣሁ ፡ መጣሁ
አሁን ፡ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ አለኝ
ጠላቴን ፡ አስወግድልኝ
የአንተ ፡ ነኝ ፡ የአንተ ፡ ብቻ
አሁን ፡ መጣሁ ፡ ተቀበለኝ
|