ያልደረስሁበት ፡ አክሊል ፡ አለኝ (Yaldereskubet Aklil Alegn)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ያልደረስሁበት ፡ አክሊል ፡ አለኝ
ኦ ፡ አምላኬ ፡ አሳስበኝ
በምድርም ፡ እንዳይጠፋብኝ
ስታክት ፡ ና ፡ አስጠንቅቀኝ

ያልደረስሁበት ፡ ርስትም ፡ አለኝ
እንዳላባክነው ፡ እርዳኝ
በወጽመዱም ፡ እንዳያጸምደኝ
ከሰይጣን ፡ ተንኮል ፡ ጠብቀኝ

ኦ ፡ ጌታዬ ፡ ኦ ፡ የሞትህልኝ
በቅዱስ ፡ እጅህ ፡ ደግፈኝ
ወደ ፡ ሰማይም ፡ ስታደርሰኝ
ያን ፡ ቅዱስ ፡ አክሊሌን ፡ ስጠኝ