ያፈሰስህልን ፡ ደምህን (Yafesesihilin Demihin)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ያፈሰስህልን ፡ ደምህን
ኦ! ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ተመስገን
ከሰይጣን ፡ ተንኮልና ፡ ኃይል
በሞትህ ፡ አድነኸናል

ኦ! ፍፁም ፡ አምላክ ፡ ፍፁም ፡ ሰው
ና! ጸሎታችንን ፡ ስማው
የታሰርንበት ፡ ወጽመዱን
በኃይልህ ፡ በጥሰው ፡ አሁን

ከኃጢአትም ፡ ጠብቀን
መስቀል ፡ ሲከብድም ፡ ደግፈን
ጭንቅም ፡ እንዳያሸንፈን
ቅዱስ ፡ ረድዔትህን ፡ ስጠን

ኦ! ኢየሱስ ፡ ወንድማችን ፡ ነህ
በሁሉም ፡ ረድዔታችን ፡ ነህ
ከመከራችን ፡ አድነን
ከአንተም ፡ ዘንድ ፡ ሕይወትን ፡ ስጠን