ያች ፡ ታናሽ ፡ መንጋ ፡ ብፅዕት ፡ ናት (Yach Tanash Menga Bitsiet Nat)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ያች ፡ ታናሽ ፡ መንጋ ፡ ብፅዕት ፡ ናት
የክርስቶስ ፡ ቤተ ፡ ሰው
ጠላትም ፡ ቢያስጨንቃት
እረኛዋም ፡ ታላቅ ፡ ነው
ከመከራ ፡ ያድናታል
በቃሉም ፡ ያበረታታል
ወዳገሩም ፡ ይመራታል
በእጁም ፡ ይይዛታል

በጐቹንም ፡ ያውቃቸዋል
እነርሱም ፡ አወቁት
ልባቸውም ፡ አዲስ ፡ ሆኗል
ቃሉንም ፡ አመኑት
በመንፈስ ፡ ኃይልና ፡ ብርሃን
ከፍርድ ፡ ከሰይጣንም ፡ ሥልጣን
ተቀበሉ ፡ ምሉዕ ፡ መዳን
የአምላክ ፡ ቅዱሣን

እኔስ ፡ ኦ! ኢየሱስ ፡ ያንት ፡ እሆን?
እኔንም ፡ ታውቅ ፡ ይሆን?
ተከትዬህ ፡ እሄድ ፡ ይሆን?
ታስገባኝስ ፡ ይሆን?
ኦ! ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጥያቄን
ስጠይቅ ፡ መልስ ፡ መልስህን
በበጐች ፡ መንጋ ፡ ውስጥ ፡ እኔን
ት ቆ ጥ ራ ለ ህ ን?

አቤቱ ፡ ልቤን ፡ መርምረው
ለአንተስ ፡ ይቻልሃል
በፍፁም ፡ የአንተ ፡ አድርገው
ስለርሱ ፡ ሙተሃል
ችሮታህም ፡ ሳይታወቀኝ
በሕይወትህ ፡ የገዛኸኝ
እሞት ፡ ድረስ ፡ ከወደድኸኝ
ልወድህ ፡ አስተምረኝ

ኋላም ፡ ትወደኛለህ ፡ ወይ?
ብለህ ፡ ብትጠይቀኝ
እላለሁ ፡ ቸር ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ!
አንተማ ፡ አወቅኸኝ
ድካም ፡ ቢያጐላላኝም
በኃጢአት ፡ ብጨነቅም
ልከተልህ ፡ ልወድህም
ፈቃዴስ ፡ ሆኗል

ስቸር ፡ ስፈራ ፡ ምላሼን
ልሰጥ ፡ ቢቸግረኝ
አንተስ ፡ ትላለህ ፡ ገንዘቤን
መውደድም ፡ አይቸግረኝ
በሞት ፡ በሕይወት ፡ ወደድኸኝ
ለአንተም ፡ በደምህ ፡ ዋጀኸኝ
ኦ! ቸር ፡ ወዳጄ ፡ ለአንተ ፡ ነኝ
በፊት ፡ ለወደድኸኝ