ያ ፡ ነው ፡ ደስታዬ (Ya New Destaye)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ያ ፡ ነው ፡ ደስታዬ
ያ ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ጌታዬን ፡ ሳየው ፡ ለብቻዬ (፪X)

መፃተኛ ፡ ነኝ ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ
የንጉሥ ፡ ልጅ ፡ ነኝ ፡ አገሬም ፡ በሰማይ
አምላክ ፡ በክንፉ ፡ ይጋርደኛል
ከቀትር ፡ ጋኔን ፡ ይሰውረኛል

አዝ፦ ያ ፡ ነው ፡ ደስታዬ
ያ ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ጌታዬን ፡ ሳየው ፡ ለብቻዬ (፪X)

መልካም ፡ ዘር ፡ ዘራ ፡ ጌታ ፡ በማሣው
እንክርዳድ ፡ ግን ፡ ገብቶ ፡ አበላሸው
አዳዲስ ፡ ነገር ፡ ጌታ ፡ አስተምረኝ
ለሰይጣን ፡ ዘዴ ፡ ብልህ ፡ አድርገኝ

አዝ፦ ያ ፡ ነው ፡ ደስታዬ
ያ ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ጌታዬን ፡ ሳየው ፡ ለብቻዬ (፪X)

በምድር ፡ ገጽ ፡ ሁሉ ፡ እንዲያስከብሩህ
ፀጋህን ፡ አብዛ ፡ ለአገልጋዮችህ
በድካማቸው ፡ ራራላቸው
አገልጋዮችህ ፡ ብዙዎች ፡ ናቸው

አዝ፦ ያ ፡ ነው ፡ ደስታዬ
ያ ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ጌታዬን ፡ ሳየው ፡ ለብቻዬ (፪X)