ያ ፡ አዲስ ፡ ኢየሩሣሌም (Ya Addis Eyerusalem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ያ ፡ አዲስ ፡ ኢየሩሣሌም ፡ በላይ ፡ ተሠርቷል
በዚያም ፡ ምሉ ፡ ደስታና ፡ ሰላም ፡ ይቆየኛል
በዚህ ፡ በምድር ፡ ግን ፡ ፍርሃት ፡ ሁከትም ፡ በዝቷል
ሲሻልም ፡ እንኳ ፡ መከራ ፡ ድካምም ፡ መልቷል

እንዲህ ፡ ከሆነስ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ ወደየሩሣሌም
ብናፍቅ ፡ አያስደንቅም ፣ ብመኝ ፡ አይገርመኝም
መወለዴ ፡ ከዚያ ፡ ነው ፣ ቤቴም ፡ ዝምድናዬም
በዚህም ፡ በእንግድነት ፡ ነጻነት ፡ የለኝም

በዕውነት ፡ አንድ ፡ የሣሌም ፡ ልጅ ፡ ልሆን ፡ ተወለድሁኝ
ከሰይጣን ፡ ኃይል ፣ ከሕግም ፡ ፍርድ ፡ ዓርነት ፡ ወጣሁኝ
በኢየሱሥም ፡ ለመንፈሴ ፡ መዳን ፡ ካገኘሁኝ
የአምላክ ፡ ልጅ ፡ በፀጋው ፡ ነኝ ፡ ባርያም ፡ አይደለሁኝ

ሊያድነኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ በሞተው ፡ አምኜ
በሰጠኝ ፡ ፀጋ ፡ ውስጥ ፡ ልኑር ፡ እርሱን ፡ ተማምኜ
ከዓብ ፡ ዘንድ ፡ እንደ ፡ አማላክ ፡ ከቆመ ፡ ለእኔ
በእርሱ ፡ ሲያየኝ ፡ ጻድቅ ፡ ነኝ ፡ በእርሱ ፡ በመድኅኔ

ግን ፡ በምግባር ፣ በሕግ ፡ ሥራም ፡ ሊድን ፡ ለሞከረ
ስለርሱ ፡ መድኅኑ ፡ ሲሞት ፡ በከንቱ ፡ ነበረ
በዕምነት ፡ ጻድቅ ፡ እንዲድን ፡ ነቢዩ ፡ ነገረ
በክርስቶስ ፡ ሞት ፡ ምሉ ፡ መዳን ፡ ለእኛ ፡ ተፈጠረ

ስለእኔ ፡ ነፍሱን ፡ ለውጦ ፡ ፍፁም ፡ በወደደኝ
በእኔም ፡ አይደል ፡ በክርስቶስ ፡ ግን ፡ ሕያው ፡ በዕምነት ፡ ነኝ
ከእርሱም ፡ ጋር ፡ ተሰቅዬ ፡ መናኝ ፡ በዓለም ፡ ነኝ
የዓለምም ፡ ወዳጅ ፡ ልሆን ፡ አሁን ፡ ምን ፡ ጠንቅ ፡ አለኝ?

ወዳምላክም ፡ ከተማ ፡ ስደርስ ፣ ከምድሩ ፡ ሥቃይ
ዕረፍት ፣ ሰላምም ፣ ደስታም ፡ ይቆየኛል ፡ በላይ
ልቅሶ ፣ መጣጣር ፣ ጩኸት ፡ አይገኝም ፡ በሰማይ
ሌትም ፡ አይሆንም ፡ ያምላክ ፡ በግ ፡ ነው ፡ ያገሩ ፡ ፀሐይ

በእንጨት ፡ የተሰቀለውን ፡ መድኃኒት ፡ ካየሁኝ
በምድር ፡ የሚወደደውን ፡ መሻት ፡ ሰለቸሁኝ
አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ ፈልጌ ፡ እርሱን ፡ ተመኘሁኝ
ወዳንቺ ፡ ኢየሩሣሌም ፡ ለመድረስ ፡ ናፈቅሁኝ