From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ወንጌል ፡ የሚለውን ፡ ሰምቼ
ደስታዬ ፡ ምሉዕ ፡ ነው
ከአምላክ ፡ ርስት ፡ ተቀብዬ
ምሥጋናዬን ፡ ልስጠው
የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ተዛምዶናል
መድኃኒታችን ፡ ሆኗል
ደስታዬም ፡ ምሉዕ ፡ ነው
አሁን ፡ የምድሩ ፡ ሕማም
በጣም ፡ ቢበዛብኝም
የልቤ ፡ ኃይል ፡ የነፍስ ፡ ሰላም
ሁሉም ፡ ቢጠፋኝም
ግን ፡ አምላክ ፡ በሰማይ ፡ ዙፋን
ሲሰጥ ፡ ለወንድሜ ፡ ሥልጣን
መዳኔ ፡ ዕርግጥ ፡ ነው
ይህ ፡ የዘለዓለም ፡ ምክር ፡ ነው
የፀጋ ፡ ምሥጢርም
የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ቤዛችን ፡ ነው
ያፈሳል ፡ ደሙንም
ኦ ፡ ግሩም ፡ የሆነ ፡ ዘመዴ
ሲሞት ፡ ጠፋልኝ ፡ ዕዳዬ
ደስታዬም ፡ ምሉዕ ፡ ነው
የአዳም ፡ ርስት ፡ በባሕሪዬ
ስወርሰው ፡ ታሠርሁ
በክርስቶስ ፡ ግን ፡ በመድኅኔ
ዓርነት ፡ ወጣሁ
የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ሰው ፡ ሆኖልኝ
ነፍሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ሊያድነኝ
ደስታዬ ፡ ምሉዕ ፡ ነው
እንዲህ ፡ ከሆነ ፡ ማመንን
ልተው ፡ አልደፍርም
የሰጠውም ፡ መሥዋዕትን
ልንቀው ፡ አልችልም
ጥፋቴ ፡ ቢበዛብኝም
ይበልጣል ፡ ግን ፡ የበጉ ፡ ደም
ደስታዬም ፡ ምሉዕ ፡ ነው
|