ወንድሞቼ ፡ እንነሣ (Wondimochie Ininesa)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ወንድሞቼ ፡ እንነሣ
እንገሥግስ ፡ በዕልልታ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ከኛ ፡ ጋራ
መስቀሉንም ፡ እንሸከም
ለመከተል ፡ ብንደክም
ሳይረዳን ፡ አይተወንም
በቅን ፡ መንገድ ፡ ይመራናል
ከጉዳት ፡ ይጠብቀናል

ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ በጀግንነት
ጦር ፡ ወደ ፡ ተፋፋመበት
እንከተል ፡ በድፍረት
በጌታ ፡ ሰንደቅ ፡ ዓላማ
ሙተን ፡ ብንራገፍ ፡ እንኳ
ከዕውነት ፡ አንዛባ
ክብሩም ፡ በኛ ፡ ይንሠራፋ
ይፈጸም ፡ የንጉሥ ፡ ተስፋ

ዓርበኞች ፡ ሁነን ፡ በፍጥነት
ብኗጋ ፡ ሊመሠረት
በዓለሙ ፡ ቅዱስ ፡ ዕውነት
የውሸት ፡ ምሽግ ፡ ሊፈርስ
ድል ፡ ሁኖ ፡ ክፋት ፡ እስኪነግሥ
ምሕረቱ ፡ በሚታይበት
ሊሰፋ ፡ የማዳን ፡ ዕውቀት

ብርቱ ፡ ጀግና ፡ ሆነ ፡ ስሙ
የተሳለ ፡ ሠይፍም ፡ ቃሉ
ታጠቀ ፡ በዕውነቱ
በሚገባ ፡ ድል ፡ ይነሣል
ሁከት ፡ በሰላም ፡ ይተካል
ሰው ፡ ከጥፋት ፡ ይድናል
የሚማቅቅ ፡ በባርነት
በእርሱ ፡ ያገኛል ፡ ዓርነት

አባቶች ፡ አሻግረው ፡ ያዩት
ጻድቃን ፡ በትንቢት ፡ የጻፉት
አንድ ፡ ጊዜ ፡ ሊታይ ፡ በግልጥ
ሕዝቡ ፡ እየቀለዱበት
የሞተ ፡ በመስቀል ፡ እንጨት
ንጉሥ ፡ ሁኖ ፡ ሊገለጥ
ለማያፍሩ ፡ በመስቀል
ከክብረቱ ፡ ሊያካፍል

ለግዛቱ ፡ እንሰለፍ
በሥራችን ፡ አንወዘፍ
ቀን ፡ በከንቱ ፡ አናሳልፍ
ብርሃኑ ፡ በማይጠፋብን
በሰማያዊ ፡ ቤታችን
ሰላም ፡ ዕረፍት ፡ ሊቆየን
ስንሻገር ፡ ከዚህች ፡ ምድር
ዕልል! ብለን ፡ እንዘምር