From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
ዘለዓለም ፡ ምስጢረኛዬ
የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
ገበናዬን ፡ አሳየዋለሁ (፪x)
ለሰው ፡ ብመስል ፡ የደላው
ውስጤ ፡ ግን ፡ እሳት ፡ ንዳድ ፡ ነው
አፌን ፡ አልከፍትም ፡ ለማንም
ጌታ ፡ ያውቃል ፡ ትርፌን ፡ ጉድለቴንም (፪x)
አዝ፦ ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
ዘለዓለም ፡ ምስጢረኛዬ
የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
ገበናዬን ፡ አሳየዋለሁ (፪x)
ድብቅ ፡ አድርጌ ፡ ምስጢሬን
አስጸያፊውን ፡ ስራዬን
እነግረዋለሁኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጊዜ ፡ የማይለውጠው (፪x)
አዝ፦ ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
ዘለዓለም ፡ ምስጢረኛዬ
የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
ገበናዬን ፡ አሳየዋለሁ (፪x)
ሳዝን ፡ ስተክዝ ፡ በኑሮ
እሰማለሁ ፡ እሮሮ
ብቸኝነት ፡ ሲያጠቃቃኝ
በኢየሱስ ፡ መጽናናት ፡ አለኝ (፪x)
አዝ፦ ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
ዘለዓለም ፡ ምስጢረኛዬ
የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
ገበናዬን ፡ አሳየዋለሁ (፪x)
አላምናቸው ፡ ወዳጆቼን
ፏደኞቼን ፡ ዘመዶቼን
ያጋልጡኛል ፡ ጠብቀው
አይችሉትም ፡ ጉዴን ፡ ተሸክመው (፪x)
አዝ፦ ወረት ፡ አያውቀው ፡ ጌታዬ
ዘለዓለም ፡ ምስጢረኛዬ
የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
ገበናዬን ፡ አሳየዋለሁ (፪x)
|