ውርደታችንን ፡ በክብር ፡ የለወጥህ (Werdetachenen Bekeber Yeleweth)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ውርደታችንን ፡ በክብር ፡ የለወጥህ
በእኛ ፡ ታናናሾች ፡ ምህረትህን ፡ የገለጥህ
ልናመሰግንህ ፡ ቆምን ፡ አምላካችን
ይኸው ፡ ምሥጋናችን ፡ ከልባችን
ሞገሳችንን ፡ አንተን ፡ ስናመሰግንህ
ምሥጋናህ ፡ ይብዛ ፡ አይነስብህ (፪x)

በጠላት ፡ ዛቻ ፡ እጅግ ፡ ተናውጠን
አቅሙ ፡ ከአቅማችን ፡ አይሎ ፡ አይተን
ከተራሮች ፡ መሃል ፡ ስንሰማ ፡ ድምጽህን
በበለጠን ፡ ፊት ፡ ባለድል ፡ ሆንን

አዝ፦ ውርደታችንን ፡ በክብር ፡ የለወጥህ
በእኛ ፡ ታናናሾች ፡ ምህረትህን ፡ የገለጥህ
ልናመሰግንህ ፡ ቆምን ፡ አምላካችን
ይኸው ፡ ምሥጋናችን ፡ ከልባችን
ሞገሳችንን ፡ አንተን ፡ ስናመሰግንህ
ምሥጋናህ ፡ ይብዛ ፡ አይነስብህ (፪x)

ግራ ፡ ቀኛችን ፡ ሁሉ ፡ ጨልሞ
ውስጣችን ፡ ከስቶ ፡ ልብ ፡ አጉረምርሞ
ያሳለፍነውን ፡ አሳልፈሃል
ዳግም ፡ እንዳይታይ ፡ አስወግዶሃል

አዝ፦ ውርደታችንን ፡ በክብር ፡ የለወጥህ
በእኛ ፡ ታናናሾች ፡ ምህረትህን ፡ የገለጥህ
ልናመሰግንህ ፡ ቆምን ፡ አምላካችን
ይኸው ፡ ምሥጋናችን ፡ ከልባችን
ሞገሳችንን ፡ አንተን ፡ ስናመሰግንህ
ምሥጋናህ ፡ ይብዛ ፡ አይነስብህ (፪x)

ምድረ ፡ በዳውን ፡ ዓለምልመሃል
ለጠወለገው ፡ ውበት ፡ ሰጥተሃል
ልንወድስህ ፡ ቋንቋ ፡ አይበቃንም
ስምህ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው ፡ አይጠገብም

አዝ፦ ውርደታችንን ፡ በክብር ፡ የለወጥህ
በእኛ ፡ ታናናሾች ፡ ምህረትህን ፡ የገለጥህ
ልናመሰግንህ ፡ ቆምን ፡ አምላካችን
ይኸው ፡ ምሥጋናችን ፡ ከልባችን
ሞገሳችንን ፡ አንተን ፡ ስናመሰግንህ
ምሥጋናህ ፡ ይብዛ ፡ አይነስብህ (፪x)

ለምስኪኖች ፡ ምንጭ ፡ አፍልቀሃል
ለተዋረድነው ፡ ሞገስ ፡ ሆነሃል
በህብረት ፡ ቅመን ፡ እንወድስ ፡ ስምህን
ሆታ ፡ ዕልልታ ፡ ይክበብ ፡ ዙፋንህን

አዝ፦ ውርደታችንን ፡ በክብር ፡ የለወጥህ
በእኛ ፡ ታናናሾች ፡ ምህረትህን ፡ የገለጥህ
ልናመሰግንህ ፡ ቆምን ፡ አምላካችን
ይኸው ፡ ምሥጋናችን ፡ ከልባችን
ሞገሳችንን ፡ አንተን ፡ ስናመሰግንህ
ምሥጋናህ ፡ ይብዛ ፡ አይነስብህ (፪x)