ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ (Wenzu Kefit Sitayeh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታመን ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል !
ጌታ ፡ ይመራሃል

የማዕበሉ ፡ ጌታ ፡ ቀድሞሃል
ተከተለኝ ፡ አይዞህ ፡ ይልሃል
ቀና ፡ ነው ፡ መንገዱ ፡ ተጽናና
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ አለና

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታመን ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል !
ጌታ ፡ ይመራሃል

ባሕሩ ፡ አፍ ፡ ለአፍ ፡ ሞልቶ
ወጀብ ፡ ሲያናውጠው ፡ በርትቶ
ሰንጥቀህ ፡ ማለፉን ፡ ብትፈራ
ቶሎ ፡ ብለህ ፡ ጌታህን ፡ ጥራ

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታመን ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል !
ጌታ ፡ ይመራሃል

ሁሉን ፡ በቃሉ ፡ ያዘዋል
ፍጥረትም ፡ ለርሱ ፡ ይታዘዛል
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከፊትህ
ጠላት ፡ ሲረፈረፍ ፡ ታያለህ

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታመን ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል !
ጌታ ፡ ይመራሃል

በባሕሩ ፡ ጉዞ ፡ ብትዝልም
አይዞህ ፡ ከመንገድ ፡ ላይ ፡ አትቀርም
ጌታህ ፡ አጠገብህ ፡ አለና
እርዳኝ ፡ በለው ፡ ጠጋ ፡ በልና

አዝ፦ ወንዙ ፡ ከፊት ፡ ሲታይህ
ቢመስልህ ፡ የሚውጥህ
ታመን ፡ ጉዞህን ፡ ቀጥል !
ጌታ ፡ ይመራሃል