ወንጌላችን ፡ ገና ፡ ድል ፡ ያደርጋል (Wengielachen Gena Del Yadergal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ወንጌላችን ፡ ገና ፡ ድል ፡ ያደርጋል
የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ገና ፡ ዓለምን ፡ ያዞራል
በአራቱም ፡ ማዕዘን ፡ ይዳረሳል
ሁሉን ፡ ይለውጣል ፡ ያሽንፋል

1. ገና ፡ የታሰሩትን ፡ ይፈታል
ሰንሰለታቸውን ፡ ይበጥሳል
በተለያየ ፡ ሱስ ፡ የታሠሩ
በዚህ ፡ ታላቅ ፡ ወንጌል ፡ ይፈታሉ

አዝ፦ ወንጌላችን ፡ ገና ፡ ድል ፡ ያደርጋል
የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ገና ፡ ዓለምን ፡ ያዞራል
በአራቱም ፡ ማዕዘን ፡ ይዳረሳል
ሁሉን ፡ ይለውጣል ፡ ያሽንፋል

2. ገና ፡ ያዘኑትም ፡ ይጽናናሉ
ለቅሷቸውን ፡ ትተው ፡ ይስቃሉ
በዚህ ፡ ታልቅ ፡ ወንጌል ፡ ተደስተው
ክብርን ፡ ይሰጣሉ ፡ ለከበረው

አዝ፦ ወንጌላችን ፡ ገና ፡ ድል ፡ ያደርጋል
የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ገና ፡ ዓለምን ፡ ያዞራል
በአራቱም ፡ ማዕዘን ፡ ይዳረሳል
ሁሉን ፡ ይለውጣል ፡ ያሽንፋል

3. ገና ፡ የታመሙት ፡ ይነሳሉ
አልጋቸውን ፡ ይዘው ፡ ይሄዳሉ
መቼ ፡ የእኛ ፡ ወንጌል ፡ የዋዛ ፡ ነው
አልጋን ፡ አሽክሞ ፡ የምያስሮጥ ፡ ነው

አዝ፦ ወንጌላችን ፡ ገና ፡ ድል ፡ ያደርጋል
የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ገና ፡ ዓለምን ፡ ያዞራል
በአራቱም ፡ ማዕዘን ፡ ይዳረሳል
ሁሉን ፡ ይለውጣል ፡ ያሽንፋል

4. ውጡ ፡ ያሉን ፡ ወደእኛ ፡ ይመጣሉ
ዝምበሉ ፡ ያሉን ፡ ሃሌሉያ ፡ ይላሉ
የወንገሉ ፡ እሳት ፡ ይወርድና
ሁሉ ፡ ይንበረከካል ፡ በምሥጋና

አዝ፦ ወንጌላችን ፡ ገና ፡ ድል ፡ ያደርጋል
የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ገና ፡ ዓለምን ፡ ያዞራል
በአራቱም ፡ ማዕዘን ፡ ይዳረሳል
ሁሉን ፡ ይለውጣል ፡ ያሽንፋል

5. ገና ፡ ወንጌላችን ፡ ይዳረሳል
ለኢትዮጵያ ፡ ሰላምን ፡ ይሰጣል
ጦሩን ፡ ክርክሩንም ፡ ይሽራል
የሰላሙ ፡ ወንጌል ፡ ብቻ ፡ ይነግሳል

አዝ፦ ወንጌላችን ፡ ገና ፡ ድል ፡ ያደርጋል
የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ገና ፡ ዓለምን ፡ ያዞራል
በአራቱም ፡ ማዕዘን ፡ ይዳረሳል
ሁሉን ፡ ይለውጣል ፡ ያሽንፋል