ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (Weletaw Ejeg Bezu New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አልችልም ፡ በቃል ፡ ልገልጸው
ተመስገን ፡ ብቻ ፡ ልበለው

ከቀራንዮ ፡ ሞት ፡ ጀምሮ ፡ እኔን ፡ እንከሞት ፡ አፍቅሮ
ነፍሴን ፡ በነፍሱ ፡ ለውጦ ፡ ደሙን ፡ በእንባ ፡ ቀይጦ
እኔን ፡ ልያበለፅግ ፡ ደህይቶ ፡ ነፍሱን ፡ ከስጋው ፡ ለይቶ
ንጹህ ፡ የደም ፡ ላብ ፡ ያላበው ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ ድካም ፡ ለእኔ ፡ ነው

አዝ፦ ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አልችልም ፡ በቃል ፡ ልገልጸው
ተመስገን ፡ ብቻ ፡ ልበለው

ይከሰኝ ፡ የነበር ፡ ባለፈው ፡ ጠላት ፡ በግንባሬ ፡ የጻፈው
የእዳዬን ፡ ጽህፈት ፡ ደምስሶ ፡ ዝገቴን ፡ አጥቦ ፡ አንፅቶ
ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ረድኤቴ ፡ ሰላሙን ፡ ሞላው ፡ በቤቴ
የከሳሼ ፡ ግንባር ፡ ተመታ ፡ እኔም ፡ ዘምራለሁ ፡ በደስታ

አዝ፦ ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አልችልም ፡ በቃል ፡ ልገልጸው
ተመስገን ፡ ብቻ ፡ ልበለው

ድካሜ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጉለቴ ፡ በፀጋው ፡ ነው ፡ አለሁ ፡ ማለቴ
በድፍረት ፡ ሥሙን ፡ መጥራቴ ፡ ጌታ ፡ የሰራውን ፡ ማውራቴ
ሰው ፡ ሆኜ ፡ በምድር ፡ መኖሬ ፡ በሰላም ፡ ውዬ ፡ ማደሬ
እግሬም ፡ ጸንቶ ፡ ሊቆም ፡ የቻለው ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ጸጋ ፡ ነው

አዝ፦ ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አልችልም ፡ በቃል ፡ ልገልጸው
ተመስገን ፡ ብቻ ፡ ልበለው