ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ (Weletaw Beza Gieta)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እንደ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነው ፡ የእኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው
ወደቀ ፡ ሲባል ፡ ጌታ ፡ የሚያነሳው
ኢየሱስ ፡ ረድቶኛል ፡ ከሁሉ ፡ አብልጦ
ከፍቶ ፡ አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ ታሪክ ፡ ለውጦ (፪x)

አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ
ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x)

አቤት ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማንን ፡ እረዳህ
አቤት ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማንን ፡ አገዝህ
አቤት ፡ ምህረትህ ፡ የገነነለት
እንደ ፡ እኔስ ፡ ማን ፡ በዛለት

አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ
ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x)

አንደበቴ ፡ ከምስጋና ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አያውቅም
ይዘምራል ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ሰለቸኝ ፡ አይልም
ደግነትህ ፡ በሕይወቴ ፡ እጅግ ፡ ስለበዛ
አሳጣኸኝ ፡ ከቶ ፡ የምለው ፡ ከምስጋና ፡ ሌላ

አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ
ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x)

አስታውሳለሁ ፡ ከምን ፡ እንዳነሳኝ
ሁሉም ፡ ሲፀየፍ ፡ እያየ ፡ ሲያልፈኝ
ቁስሌን ፡ ጠራርጐ ፡ እንባዬን ፡ ሲያብስ
አስቦ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ እንድደርስ

አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ
ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x)

ልማድህ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ ማድረግ ፡ ከብረህ ፡ የምታከብር
ትቢያ ፡ አራግፈኽ ፡ መሸላለም ፡ ማብቃት ፡ ለቁም ፡ ነገር
ስንቱ ፡ አረፈ ፡ እፎይ ፡ አለ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ሲጠጋ
አመለጠ ፡ በአንተ ፡ ጉልበት ፡ ከጠላት ፡ መንጋጋ

በምስጋና ፡ ሆ ፡ የተፈራ ፡ ዴንቅን ፡ ደግሞ ፡ ሆ ፡ የምትሰራ (፪x)

አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ (፪x)