ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ የልቤ ፡ ጓደኛ (Wedie Eyesus Yelebie Guadegna)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በአንተ ፡ ደጃፍ ፡ ላይ ፡ መጣልን ፡ መረጥኩኝ
በስቃይና ፡ ደስታ ፡ ክንዱን ፡ ስላየሁኝ
እስከዛሬ ፡ ድረስ ፡ እንዲህ ፡ የጠበቀኝ
አምናለሁ ፡ ጌታን ፡ ከእንግዲህ ፡ ላይለቀኝ

አዝ፦ ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ የልቤ ፡ ጓደኛ
አፍቃሪዬ ፡ የሕይወቴ ፡ መጽናኛ
ካላንተማ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ ከጐኔ
እናት ፡ አባቴ ፡ ነህ ፡ ደራሽ ፡ በሃዘኔ

ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምስጢሬን ፡ ተካፋይ
በመከራ ፡ ወጀብ ፡ ከእኔ ፡ የማይለይ
የእቶን ፡ እሳትም ፡ ቢነድ ፡ ሰባት ፡ እጥፍ
ታማኝ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ ፡ ቃሉን ፡ የማያጥፍ

አዝ፦ ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ የልቤ ፡ ጓደኛ
አፍቃሪዬ ፡ የሕይወቴ ፡ መጽናኛ
ካላንተማ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ ከጐኔ
እናት ፡ አባቴ ፡ ነህ ፡ ደራሽ ፡ በሃዘኔ

በዘለዓለም ፡ ፍቅሩ ፡ ወዶ ፡ የሚያጸና
እንደ ፡ እናት ፡ አንደ ፡ አባት ፡ ቀርቦ ፡ የሚያጽናና
ኃጥእ ፡ ነው ፡ ጥድቅ ፡ ነው ፡ በማለት ፡ የማይንቅ
ኢየሱስን ፡ አየሁ ፡ ከያዘ ፡ የማይለቅ

አዝ፦ ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ የልቤ ፡ ጓደኛ
አፍቃሪዬ ፡ የሕይወቴ ፡ መጽናኛ
ካላንተማ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ ከጐኔ
እናት ፡ አባቴ ፡ ነህ ፡ ደራሽ ፡ በሃዘኔ

ይህ ፡ በስባሽ ፡ ሥጋዬ ፡ በነገሮች ፡ ቢያዝንም
በማግኘት ፡ በማጣት ፡ ጌታን ፡ አልለውጥም
እግዚአብሔር ፡ አምላኬን ፡ ሁሌ ፡ እባርካለሁ
እንደ ፡ እርሱ ፡ የልብ ፡ ወዳጅ ፡ ከየት ፡ አገኛለሁ

አዝ፦ ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ የልቤ ፡ ጓደኛ
አፍቃሪዬ ፡ የሕይወቴ ፡ መጽናኛ
ካላንተማ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ ከጐኔ
እናት ፡ አባቴ ፡ ነህ ፡ ደራሽ ፡ በሃዘኔ