ውዴ ፡ ኢየሱስ (Wedie Eyesus)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ እዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ እዘምራለሁ

አስራ ፡ ሁለት ፡ አመት ፡ ደም ፡ እየፈሰሰኝ
ተነጥዬ ፡ መኖር ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ የራቀኝ
ከእንግዲህ ፡ ወዲያ ፡ ተስፋዬ ፡ ምንድን ፡ ነው
ዕድሜዬ ፡ በሙሉ ፡ በለቅሶ ፡ ሊያልቅ ፡ ነው
ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ሃሳቤን
ስጠብቀው ፡ ፍጻሜዬን
ድንገት ፡ ብርሃን ፡ ወጣልኝ
አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ መጣልኝ

አዝውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ እዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ እዘምራለሁ

ግርግሩ ፡ በዝቶ ፡ የሚጋፋው ፡ ሰው
አዳኜ ፡ ኢየሱስን ፡ እንዴት ፡ ላግኘው
ተስፋ ፡ በዓለመቁረጥ ፡ እየተንፏቀኩኝ
እጄን ፡ ሰደድኩና ፡ ቀሚሱን ፡ ነካሁኝ
ነካ ፡ ባረገው ፡ ነካኝ
ኃይልም ፡ ወጣና ፡ ዳንኩኝ
ታዲያ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ይህን ፡ ጌታ
አመስግኑልኝ ፡ በዕልልታ

አዝውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ እዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ እዘምራለሁ

ዘመናት ፡ አልፉ ፡ ሆኜ ፡ በጭንቀት
ለደሜ ፡ ማድረቂያ ፡ ጠፍቶ ፡ መድሃኒት
ማንም ፡ አይጠጋኝ ፡ እርኩስ ፡ ናት ፡ ተብዬ
አሁንስ ፡ መረረኝ ፡ ገላግለኝ ፡ ጌታዬ
ብዬ ፡ ሞቴንም ፡ ስጠብቅ
በሽታዬ ፡ አርጐኝ ፡ ድቅቅ
መሲሁ ፡ መጣልኝና
አቆመኝ ፡ ፈወሰኝና

አዝውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ እዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ እዘምራለሁ

ትድናለች ፡ ብሎ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ገመተኝ
ሁሉም ፡ በሩቅ ፡ ሲሸሽ ፡ ጀርባውን ፡ ሲሰጠኝ
አስታማሚ ፡ አጥቼ ፡ የሚደግፈኝ
ኢየሱስ ፡ ሲጐበኘኝ ፡ በዛ ፡ የሚያጅበኝ
የሸሹኝ ፡ ሁሉ ፡ አቀፉኝ
የናቁኝም ፡ አከበሩኝ
መሸማቀቄም ፡ ቀረልኝ
ኢየሱስ ፡ ይመስገንልኝ

አዝውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ እዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ እዘምራለሁ