ወደ ፡ ፅዮን ፡ እንጓዝ (Wede Tsion Eneguaz)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ያምላክ ፡ ወዳጆች ፡ ኑ
ደስታችሁ ፡ ትታወቅ
ኑ ፡ በአንድነት ፡ እንዘምር
ላምላካችን ፡ ቅዱስ ፡ መዝሙር
የእርሱን ፡ ዙፋን ፡ ከበን
እናንግሠው ፡ በክብር

አዝማች
ወደ ፡ ፅዮን ፡ እንጓዝ
ወደዚያች ፡ ኢየሩሣሌም
እንገሥግስ ፡ ወደ ፡ ፅዮን
ወደ ፡ አምላካችን ፡ ከተማ

እናንተ ፡ እምቢተኞች ፡ ተነሱ ፡ ዘምሩ
የእኛን ፡ አምላክ ፡ የማታውቁ ፡ ኑ
ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ታረቁ
የጌታ ፡ ልጆች ፡ ግን
ደስታችሁ ፡ ትታወቅ

አዝማች
ወደ ፡ ፅዮን ፡ እንጓዝ
ወደዚያች ፡ ኢየሩሣሌም
እንገሥግስ ፡ ወደ ፡ ፅዮን
ወደ ፡ አምላካችን ፡ ከተማ

እንግዲህ ፡ እንዘምር ፡ እንባችንም ፡ ይድረቅ
በአማኑኤል ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ነን
ድንገት ፡ ፈርተን ፡ እንዳንወድቅ
ስንጓዝ ፡ ወደርሱ
ወዳማረው ፡ አገር

አዝማች
ወደ ፡ ፅዮን ፡ እንጓዝ
ወደዚያች ፡ ኢየሩሣሌም
እንገሥግስ ፡ ወደ ፡ ፅዮን
ወደ ፡ አምላካችን ፡ ከተማ