ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ስገባ (Wede Meqdesu Segeba)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አንድ ፡ ጊዜ ፡ አይደለም ፡ ሁለት ፡ ጊዜ
ጌታ ፡ የመከረኝ ፡ በግሳፄ
እንደ ፡ እኔማ ፡ ቢሆን ፡ እንደ ፡ ኃጢአቴ
የቁጣ ፡ ልጅ ፡ ነበርኩ ፡ ከፍጥረቴ

ዛሬ ፡ ግን ፡ መክሮኝ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ (፪x)
በመቅደሱ ፡ ውስጥ ፡ አዜማለሁ

አዝ፦ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ስገባ
ደምጼን ፡ ላሰማ ፡ በምሥጋና
በፍቅሩ ፡ ስቦ ፡ የመከረኝን
ባማረ ፡ ሥፍራ ፡ ያስቀመጠኝን
ከፍ ፡ ላድርገው ፡ እግዚአብሔርን

አሁን ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ ከኋላ ፡ ሳየው
መራራው ፡ ሕይወት ፡ ዛሬ ፡ የጣፈጠው
እንዴት ፡ ያለውን ፡ ሰውን ፡ ለወጥኸው?
አምላኬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ስራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው

ገመድ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ ፡ ወድቃልኝ
በአምላኬ ፡ ርስቴ ፡ ተዋባችልኝ (፪x)

አዝ፦ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ስገባ
ደምጼን ፡ ላሰማ ፡ በምሥጋና
በፍቅሩ ፡ ስቦ ፡ የመከረኝን
ባማረ ፡ ሥፍራ ፡ ያስቀመጠኝን
ከፍ ፡ ላድርገው ፡ እግዚአብሔርን

አንካሳ ፡ ነበርኩ ፡ መሄድ ፡ የማልችል
እውርም ፡ ነበርኩ ፡ ማየት ፡ የማልችል
ኢየሱስ ፡ የሚባል ፡ አንድ ፡ ወዳጅ ፡ አይቶኝ
በእጆቹ ፡ ዳሶኝ ፡ በድንቅ ፡ ፈወሰኝ

እንደርሱ ፡ ያለ ፡ የለኝምና
ዛሬም ፡ ቆሜያለሁ ፡ በምሥጋና (፪x)

አዝ፦ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ስገባ
ደምጼን ፡ ላሰማ ፡ በምሥጋና
በፍቅሩ ፡ ስቦ ፡ የመከረኝን
ባማረ ፡ ሥፍራ ፡ ያስቀመጠኝን
ከፍ ፡ ላድርገው ፡ እግዚአብሔርን