ወደ ፡ መቅደሱ ፡ እንገባለን (Wede Meqdesu Engebalen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ እንገባለን
ምስጋና ፡ ዝማሬን ፡ እልልታን ፡ ይዘን
አሜን ፡ ክብር ፡ ይሁን (፬x)

እናሸበሽባለን ፡ ደስ ፡ እያለን
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንዲሆን ፡ ክብር ፡ ይሁን (፬x)

1. ከነፍሳችን ፡ ምስጋና (፪x)
ከበሮና ፡ በገና (፪x)
ይዘን ፡ እንገባለን ፡ በአንድነት ፡ ሆነን ፡ በሰማይ ፡ በምድር
ሥሙን ፡ ልናከብር (፪x)

አዝ፦ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ እንገባለን
ምስጋና ፡ ዝማሬን ፡ እልልታን ፡ ይዘን
አሜን ፡ ክብር ፡ ይሁን (፬x)

እናሸበሽባለን ፡ ደስ ፡ እያለን
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንዲሆን ፡ ክብር ፡ ይሁን (፬x)

2. ማህተሙን ፡ ለፈታ (፪x)
ለይሁዳ ፡ አንበሳ (፪x)
ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ አንዳችም ፡ ሳናስቀር
እንሰዋለታለን ፡ ጠላት ፡ እስክሸበር (፪x)

አዝ፦ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ እንገባለን
ምስጋና ፡ ዝማሬን ፡ እልልታን ፡ ይዘን
አሜን ፡ ክብር ፡ ይሁን (፬x)

እናሸበሽባለን ፡ ደስ ፡ እያለን
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንዲሆን ፡ ክብር ፡ ይሁን (፬x)

3. ከእግሮቹ ፡ ሥር ፡ ተደፍተን (፪x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያልን (፪x)
እንስገድለታለን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ በግ
አውጥቶልናልና ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ ከረግረግ (፪x)

አዝ፦ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ እንገባለን
ምስጋና ፡ ዝማሬን ፡ እልልታን ፡ ይዘን
አሜን ፡ ክብር ፡ ይሁን (፬x)

እናሸበሽባለን ፡ ደስ ፡ እያለን
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንዲሆን ፡ ክብር ፡ ይሁን (፬x)