ወደ ፡ መቅደስ ፡ ተራሮች (Wede Meqdes Teraroch)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ወደ ፡ መቅደስ ፡ ተራሮች ፡ ዓይኔን ፡ አነሳለሁ
ረድኤት ፡ ከጌታ ፡ አለኝ ፡ በፍቅሩ ፡ አምናለሁ
ረድኤት ፡ ይመጣልኛል ፡ ሁሉን ፡ ከፈጠረ
ጸሎቴ ፡ ትሰማልኛለች ፡ በርህሩሁ ፡ ጌታ

እግሮቼን ፡ ለመናወጥ ፡ አሳልፎ ፡ አይሰጥም
ጠባቂዬ ፡ በእርግጥ ፡ ከቶ ፡ አይደክመውም
እርሱ ፡ ፀጋውን ፡ ሰጠኝ ፡ ከኃጢአት ፡ ለማዳን
ዘወትር ፡ ሊቆምልኝ ፡ እስክደርስ ፡ ወደላይ

አምላክ ፡ ነፍሴን ፡ ከክፉ ፡ አሁን ፡ ይጠብቃል
ያደረገልኝ ፡ ሁሉ ፡ ጥቅም ፡ ይሆነኛል
መግባቴን ፡ ይባርካል ፡ ድምድሙን ፡ ያቀናል
በአምላክ ፡ ለሚማጠን ፡ ለግሶ ፡ ይሰጣል