ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እቀርባለሁ (Wede Eyesus Eqerbalehu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እቀርባለሁ ፡ ባለበት ፡ እኖራለሁ
ለማገልገል ፡ እየሞከርኩ ፡ በእጁ ፡ እድናለሁ

አዝ፦ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እቀርባለሁ
ወደ ፡ እርሱ ፡ እቀርባለሁ
ሕይወቴን ፡ እሰጠዋለሁ
ወደ ፡ እርሱ ፡ እቀርባለሁ

ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እቀርባለሁ ፡ የምሰውረው ፡ የለም
እንደሚወደኝ ፡ አውቃለሁ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እቀርባለሁ

አዝ፦ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እቀርባለሁ
ወደ ፡ እርሱ ፡ እቀርባለሁ
ሕይወቴን ፡ እሰጠዋለሁ
ወደ ፡ እርሱ ፡ እቀርባለሁ

ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እቀርባለሁ ፡ ብርታቱንም ፡ እሻለሁ
ደግነቱን ፡ አወራለሁ ፡ በደስታ ፡ እሠራለሁ

አዝ፦ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እቀርባለሁ
ወደ ፡ እርሱ ፡ እቀርባለሁ
ሕይወቴን ፡ እሰጠዋለሁ
ወደ ፡ እርሱ ፡ እቀርባለሁ