ወደ ፡ ቤት ፡ መጣሁ (Wede Biet Metahu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከአምላክ ፡ ርቄ ፡ ዞሬያለሁ
አሁን ፡ ተመለስሁ
በሃጥያት ፡ መንገድ ፡ ሄጃለሁ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ መጣሁ

አዝ፦ ወደ ፡ ቤት ፡ መጣሁኝ
አልዞርም ፡ በቃኝ
እጆችህን ፡ ዘርጋልኝ
ጌታ ፡ መጣሁኝ

ክቡር ፡ ዘመናት ፡ አባከንሁ
አሁን ፡ ተመለስሁ
በመራር ፡ እንባ ፡ ተጸጸትሁ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ መጣሁ

አዝ፦ ወደ ፡ ቤት ፡ መጣሁኝ
አልዞርም ፡ በቃኝ
እጆችህን ፡ ዘርጋልኝ
ጌታ ፡ መጣሁኝ

በኃጢአቴ ፡ ብዛት ፡ ደከምሁ
አሁን ፡ ተመለስሁ
ቃልህን ፡ ፍቅርህን ፡ አምናለሁ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ መጣሁ

አዝ፦ ወደ ፡ ቤት ፡ መጣሁኝ
አልዞርም ፡ በቃኝ
እጆችህን ፡ ዘርጋልኝ
ጌታ ፡ መጣሁኝ

የሚያነጻ ፡ ደምህን ፡ ስጠኝ
አሁን ፡ ተመለስሁ
ከበረዶ ፡ አብልጠህ ፡ አንጻኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ መጣሁ

አዝ፦ ወደ ፡ ቤት ፡ መጣሁኝ
አልዞርም ፡ በቃኝ
እጆችህን ፡ ዘርጋልኝ
ጌታ ፡ መጣሁኝ