From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል ፡ ጌታ
ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል
በዓለም ፡ ዞረናል ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ አይተናል
ዕርካታን ፡ ለማግኘት ፡ ስንል ፡ ተንከራተናል
ይቅር ፡ በለን ፡ ተቀበለን ፡ እባክህን ፡ አንተን ፡ በድለናል
ጉስቁልናን ፡ ተሞልተናል ፡ እጅግም ፡ ረክሰናል
ታላቁን ፡ መዳን ፡ በመናቅ ፡ መከራ ፡ ጠግበናል
ውኃ ፡ አልባ ፡ ጉድጓዶችን ፡ ለራሣችን ፡ ቆፍረናል
ከሕይወት ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ ርቀን ፡ በጥማት ፡ ደርቀናል
አዝ፦ ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል ፡ ጌታ
ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል
በዓለም ፡ ዞረናል ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ አይተናል
ዕርካታን ፡ ለማግኘት ፡ ስንል ፡ ተንከራተናል
ይቅር ፡ በለን ፡ ተቀበለን ፡ እባክህን ፡ አንተን ፡ በድለናል
የዚህ ፡ ዓለም ፡ ጉስቁልና ፡ ሰልችቶን ፡ መርሮናል
አቅጣጫ ፡ ቀይረን ፡ ከጥፋታችን ፡ መጥተናል
ሰማይና ፡ ምድር ፡ በኢየሱስ ፡ ደም ፡ ታርቀዋል
የጥልም ፡ ግድግዳ ፡ ደግሞ ፡ መፍረሱን ፡ ሰምተናል
አዝ፦ ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል ፡ ጌታ
ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል
በዓለም ፡ ዞረናል ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ አይተናል
ዕርካታን ፡ ለማግኘት ፡ ስንል ፡ ተንከራተናል
ይቅር ፡ በለን ፡ ተቀበለን ፡ እባክህን ፡ አንተን ፡ በድለናል
ለማይረባ ፡ ነገር ፡ ብለን ፡ ክብራችንን ፡ ለወጥን
ለጥፋት ፡ ምሣሌ ፡ መተረቻ ፡ መዘባበቻ ፡ ሆንን
ግን ፡ እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ ወዳንተ ፡ መራኸን
መጋረጃን ፡ ቀደህ ፡ ወደ ፡ መቅደስህ ፡ ጋበዝኸን
አዝ፦ ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል ፡ ጌታ
ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል
በዓለም ፡ ዞረናል ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ አይተናል
ዕርካታን ፡ ለማግኘት ፡ ስንል ፡ ተንከራተናል
ይቅር ፡ በለን ፡ ተቀበለን ፡ እባክህን ፡ አንተን ፡ በድለናል
እንደ ፡ ጥፋታችን ፡ ከቶ ፡ አልመለስክብንም
ዕድፈታችንንም ፡ አይተህ ፡ አልተጸየፍከንም
በደምህ ፡ አጥበኸን ፡ ዛሬ ፡ ሕይወት ፡ እንሸታለን
ስለ ፡ ምሕረትህ ፡ ምሥጋና ፡ በደስታ ፡ ዕልል ፡ እንበል
አዝ፦ ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል ፡ ጌታ
ወደ ፡ አንተ ፡ መጥተናል
በዓለም ፡ ዞረናል ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ አይተናል
ዕርካታን ፡ ለማግኘት ፡ ስንል ፡ ተንከራተናል
ይቅር ፡ በለን ፡ ተቀበለን ፡ እባክህን ፡ አንተን ፡ በድለናል
|