ወደ ፡ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ (Wede Ante Eyesus Hoy)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ወደ ፡ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ልቤ ፡ ይናፍቃል
የአምላክ ፡ በግ ፡ ሁነህ
ስለእኔ ፡ ሙተሃል

ሰላም ፡ ለእኔ ፡ ሰጠህ
ተሸክመህ ፡ ቅጣት
ጠባቂዬም ፡ ሁነህ
አወጣኸኝ ፡ ከሞት

ለእኔም ፡ ባባቴ ፡ ቤት
ሥፍራ ፡ አዘጋጀህ
ዓይናችን ፡ ያላየው
ብርሃኑም ፡ አንተ ፡ ነህ

ከዓለም ፡ መሄዴ
በደረሰ ፡ ጊዜ
ምራኝ ፡ በብርሃንህ
ልገባ ፡ አገሬ