ዋጋ ፡ ያስከፍላልና ፡ ክርስትና (Waga Yaskefelalena Kerestena)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ዋጋ ፡ ያስከፍላልና ፡ ክርስትና
ገና ፡ ምኑ ፡ ተያዘና
የአባቶቼን ፡ ወግ ፡ አይቼ
የነቢያትና ፡ የሃዋርያትን ፡ ጽዋ ፡ ጠጥቼ
ሽልማቴን ፡ እቀበላለሁ ፡ ገና ፡ ዋጋን ፡ እከፍላለሁ

የቀድሞ ፡ ነቢያትና ፡ ሃዋርያት ፡ ደምና ፡ እምባ
ታስቦ ፡ በፊትህ ፡ ዋጋ ፡ አግኝቷልና ፡ አባባ
ዛሬ ፡ በእምነት ፡ ቆሜ ፡ እጠብቃለሁ
ዋጋ ፡ ከፍዬበት ፡ አክሊሌን ፡ እወስዳለሁ

አዝ፦ ዋጋ ፡ ያስከፍላልና ፡ ክርስትና
ገና ፡ ምኑ ፡ ተያዘና
የአባቶቼን ፡ ወግ ፡ አይቼ
የነቢያትና ፡ የሃዋርያትን ፡ ጽዋ ፡ ጠጥቼ
ሽልማቴን ፡ እቀበላለሁ ፡ ገና ፡ ዋጋን ፡ እከፍላለሁ

ዋጋ ፡ ያስከፍላል ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ ፡ ኑሮ
በዓለም ፡ ተሰዶ ፡ ተጐሳቁሎ ፡ ተባሮ
የሕይወትን ፡ አክሊል ፡ ለመቀበል
ላለፉት ፡ ለእኔም ፡ ዋጋ ፡ ያስከፍላል

አዝ፦ ዋጋ ፡ ያስከፍላልና ፡ ክርስትና
ገና ፡ ምኑ ፡ ተያዘና
የአባቶቼን ፡ ወግ ፡ አይቼ
የነቢያትና ፡ የሃዋርያትን ፡ ጽዋ ፡ ጠጥቼ
ሽልማቴን ፡ እቀበላለሁ ፡ ገና ፡ ዋጋን ፡ እከፍላለሁ

የጽድቅና ፡ የድል ፡ አክሊል ፡ በላይ ፡ ተዘጋጅቶ
ከጌታ ፡ መቀበል ፡ ለወንጌል ፡ እምነቴም ፡ ፀንቶ
በእግር ፡ ግንድ ፡ እስራት ፡ ተጨንቄ
ብድራቴን ፡ ከእጁ ፡ እወስዳለሁ ፡ ማቅቄ

አዝ፦ ዋጋ ፡ ያስከፍላልና ፡ ክርስትና
ገና ፡ ምኑ ፡ ተያዘና
የአባቶቼን ፡ ወግ ፡ አይቼ
የነቢያትና ፡ የሃዋርያትን ፡ ጽዋ ፡ ጠጥቼ
ሽልማቴን ፡ እቀበላለሁ ፡ ገና ፡ ዋጋን ፡ እከፍላለሁ

በድንጋይ ፡ ውግራት ፡ በመጋዝ ፡ ተሰንጥቄ
በዘይት ፡ ቅቅላት ፡ በአንበሳ ፡ አፍ ፡ ተነጥቄ
ሽልማቴም ፡ የክብር ፡ አክሊል ፡ ነው
ከአብላክ ፡ እጅ ፡ ልቀበል ፡ ጊዜያቱ ፡ ቅርብ ፡ ነው

አዝ፦ ዋጋ ፡ ያስከፍላልና ፡ ክርስትና
ገና ፡ ምኑ ፡ ተያዘና
የአባቶቼን ፡ ወግ ፡ አይቼ
የነቢያትና ፡ የሃዋርያትን ፡ ጽዋ ፡ ጠጥቼ
ሽልማቴን ፡ እቀበላለሁ ፡ ገና ፡ ዋጋን ፡ እከፍላለሁ