ፅኑ ፡ ጦር ፡ ብርቱ ፡ ኃይል (Tsenu Tor Birtu Hayl)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

 
1. ጋሻ ፡ ጦሩን ፡ ይዞ ፡ ሰይፉን ፡ መዞባቸው
ነፍሴን ፡ ከምዋጉአት ፡ ጌታ ፡ ተዋጋቸው
የጦር ፡ ሜዳ ፡ አዝማች ፡ ቆራጥ ፡ ጦረኛ ፡ አለኝ
እግዚአብሔር ፡ ተነሳ ፡ ሠይፉን ፡ መዘዘልኝ

አዝ፦ ፅኑ ፡ ጦር ፡ ብርቱ ፡ ኃይል ፡ ከጌታ
ጠላቴን ፡ አሳዶ ፡ ምሽግ ፡ የሚመጣ
ጋሻውን ፡ አንግቦ ፡ ሠይፉን ፡ ነቀነቀ
ይህን ፡ ሲያይ ፡ ጠላቴ ፡ በቅፅበት ፡ ወደቀ

2. የአሳዳጄን ፡ መንገድ ፡ በሰይፍ ፡ ስለት ፡ ዘጋ
ጉዳቴን ፡ የማይወድ ፡ ጌታ ፡ እጁን ፡ ዘረጋ
የከበቡኝ ፡ ፡ ሁሉ ፡ ኃፍረት ፡ ከበባቸው
የጌታ ፡ እየሱስ ፡ ደም ፡ ስለ ፡ ተዋጋቸው

አዝ፦ ፅኑ ፡ ጦር ፡ ብርቱ ፡ ኃይል ፡ ከጌታ
ጠላቴን ፡ አሳዶ ፡ ምሽግ ፡ የሚመጣ
ጋሻውን ፡ አንግቦ ፡ ሠይፉን ፡ ነቀነቀ
ይህን ፡ ሲያይ ፡ ጠላቴ ፡ በቅፅበት ፡ ወደቀ

3. የመላእክት ፡ ጠባቂ ፡ አምላኬ ፡ ሰጥቶኛል
የደም ፡ እሳት ፡ ቅጥር ፡ ዙሪያዬን ፡ ከቦኛል
የስውር ፡ ጦር ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ የሰጠኝ
ሁሉን ፡ እችላለሁ ፡ ሐይልን ፡ በሚሰጠኝ

አዝ፦ ፅኑ ፡ ጦር ፡ ብርቱ ፡ ኃይል ፡ ከጌታ
ጠላቴን ፡ አሳዶ ፡ ምሽግ ፡ የሚመጣ
ጋሻውን ፡ አንግቦ ፡ ሠይፉን ፡ ነቀነቀ
ይህን ፡ ሲያይ ፡ ጠላቴ ፡ በቅፅበት ፡ ወደቀ

4. ጦር ፡ ሜዳው ፡ ስጋየም ፡ ምሽጌም ፡ እምነት ፡ ነው
መዋጊያዬ ፡ ቃሉ ፡ ስለታም ፡ ሰይፍ ፡ ነው
በጌታ ፡ እየሱስ ፡ ስም ፡ ምሽግ ፡ እሰብራለሁ
ኃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ

አዝ፦ ፅኑ ፡ ጦር ፡ ብርቱ ፡ ኃይል ፡ ከጌታ
ጠላቴን ፡ አሳዶ ፡ ምሽግ ፡ የሚመጣ
ጋሻውን ፡ አንግቦ ፡ ሠይፉን ፡ ነቀነቀ
ይህን ፡ ሲያይ ፡ ጠላቴ ፡ በቅፅበት ፡ ወደቀ