ጸሐዩ ፡ ሊገባ ፡ ነው (Tsehayu Ligeba New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ፀሐዩ ፡ ሊገባ ፡ ነው
ጨለማ ፡ ሊመጣ ፡ ነው
ትጋ ፡ ስገድ ፡ ጸልይም
የሌሊት ፡ ጸዳል ፡ ሲታይ ፡ በሰማያት

አዝማች
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ልዑል ፡ አምላክ
በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሠራዊት ፡ ያመስግኑህ
ልዑል ፡ አምላክ

አንተ ፡ የሕይወት ፡ ጌታ
የምትሰጠን ፡ ደስታ
እርዳን ፡ ፊትህን ፡ ስንሻ
በፍቅር ፡ እጅህ ፡ ያዘን
ና ፡ ቅረበን

አዝማች
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ልዑል ፡ አምላክ
በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሠራዊት ፡ ያመስግኑህ
ልዑል ፡ አምላክ

ሲመጣ ፡ የሞት ፡ ጽላ
ጸጋህ ፡ አብዝቶ ፡ ይሙላ
ፍቅርህና ፡ ሕይወትህ ፡ ያብራልን
በምሕረትህ ፡ በልባችን

አዝማች
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ልዑል ፡ አምላክ
በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሠራዊት ፡ ያመስግኑህ
ልዑል ፡ አምላክ

ኮከብ ፡ ጨረቃም ፡ ጸሐይ
ሲጠፋ ፡ ከዓለም ፡ ላይ
ግርማህ ፡ በኛ ፡ ላይ ፡ በራ
ጨለማም ፡ ሁሉ ፡ ይጥፋ ፡ ለዘለዓለም

አዝማች
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ልዑል ፡ አምላክ
በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሠራዊት ፡ ያመስግኑህ
ልዑል ፡ አምላክ