ፀሐይ ፡ ወጣ ፡ አሁን ፡ ንቁ (Tsehay Wotta Ahun Niqu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ፀሐይ ፡ ወጣ ፡ አሁን ፡ ንቁ
ድል ፡ ይነሣል ፡ ብርሃኑ
ሕዝቦች ፡ በወንጌል ፡ ሊሳቡ
ኢየሱስን ፡ ሊያመልኩ ።

አሁን ፡ አምላካዊ ፡ ግርማ
በምድራችን ፡ ላይ ፡ ወጣ
ሌት ፡ ሲጨረስ ፡ ቀን ፡ ሲበራ
እናመስግን ፡ በደስታ ።

አሁን ፡ ንጉሡ ፡ ይመጣል
ሕዝቡንም ፡ ያስከትታል
አሕዛብንም ፡ ይጠራል
ከብፅዕናው ፡ ያድላል ።

እላንት ፡ ሕዝቦች ፡ አሁን ፡ እዩ!
ልጆቻችሁ ፡ ሲመጡ
ወደ ፡ ንጉሥ ፡ ሠርግ ፡ ሊገቡ
ነጭ ፡ ሐር ፡ ልብስ ፡ ተከናነቡ ።

ቆነጃጅታችሁ ፡ ወጡ
ንጉሡን ፡ ሊቀበሉ
ሕፃናት ፡ ያከብራሉ
ስለ ፡ ፍቅሩ ፡ ሲሰሙ ።

ወድሱት ፡ አምላክ ፡ ይጸናል
በሰጠን ፡ የተስፋ ፡ ቃል
ተክሉን ፡ በምሕረት ፡ ያለማል
ዘወትር ፡ ይቆምልናል ።

ሥራውን ፡ ዕርግጥ ፡ ሊፈጽም
አንድ ፡ እንኳ ፡ አይወዝፍም
ግርማው ፡ ይታይ ፡ በዓለም
ይመስገን ፡ ለዘለዓለም ።