ፀጋህን ፡ ስጠኝ (Tsegahen Setegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ፀጋህን ፡ ስጠኝ
በእጅህም ፡ ምራኝ
ኦ ፡ ቸር ፡ ሰማያዊ ፡ አባት
እንዳይደልለኝ
ከዓለም ፡ ጠብቀኝ
አገሬ ፡ እስክገባባት
የመድኃኒታችን ፡ አካል ፡ እንድሆን
በዕውነት ፡ በእርሱ ፡ የምገኝም ፡ እንድሆን
ፀጋህን ፡ ስጠኝ
በጅህም ፡ ምራኝ
ኦ ፡ ቸር ፡ ሰማያዊ ፡ አባት

ዕምነት ፡ ፈጥረህ
ኃይልም ፡ ጨምረህ
ና ፡ የፈቀድኸውን ፡ እዘዘኝ
አዘህ ፡ መክረህ
አቅም ፡ ፈጥረህ
ለመታዘዝም ፡ አግዘኝ
ልቤም ፡ አንተን ፣ አምላክ ፡ ብቻ ፡ በመፍራት
ልትኖር ፡ በፀጋህ ፡ ወትሮ ፡ ጠብቃት
ዕምነት ፡ ለኩሰህ
ኃይልም ፡ ለግሰህ
ና ፡ የፈቀድኸውን ፡ እዘዘኝ