ፀጋህ ፡ ይብዛልኝ ፡ ለክብርህ ፡ አቁመኝ (Tsegah Yebzalegne Lekebreh Aqumegne)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. አዲስ ፡ ነገር ፡ ልይ ፡ ኃይልህ ፡ ሲሞላኝ
እራሴን ፡ ስረሳው ፡ ስትታይብኝ
ክብሬ ፡ ትዘምር ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ዳዊት
መንፈስህ ፡ ይስራ ፡ ይለፍ ፡ በሙላት

አዝ፦ ፀጋህ ፡ ይብዛልኝ ፡ ለክብርህ ፡ አቁመኝ
ላገልግልህ ፡ ጉልበቴን ፡ አድስ (፫x)

2.ትምክህቴን ፡ ከእኔ ፡ ዛሬ ፡ ቁረጠው
አውቃለሁ ፡ ባይ ፡ ነኝ ፡ ኃይሌን ፡ ውሰደው
በብርታቴ ፡ አይሆንም ፡ የአንተ ፡ ሥራ
ጉልበቴን ፡ አድስ ፡ መንፈስህ ፡ ይሥራ

አዝ፦ ፀጋህ ፡ ይብዛልኝ ፡ ለክብርህ ፡ አቁመኝ
ላገልግልህ ፡ ጉልበቴን ፡ አድስ (፫x)

3. ፀጋህን ፡ ስጠኝ ፡ በድፍረት ፡ ልውጣ
ሞገስም ፡ ሁነኝ ፡ ጠላቴ ፡ ይረታ
ላገለግልህ ፡ ክብሩ ፡ ላንተ ፡ ይሁን
ኃይሌም ፡ ይታደስ ፡ ምርኮንም ፡ ላግኝ

አዝ፦ ፀጋህ ፡ ይብዛልኝ ፡ ለክብርህ ፡ አቁመኝ
ላገልግልህ ፡ ጉልበቴን ፡ አድስ (፫x)

4. ማሲንቆ ፡ ላንሳ ፡ ልነሳ ፡ እኔም
ለወዳጄ ፡ ስል ፡ የሚያግደኝ ፡ የለም
እነሆ ፡ ይኸው ፡ ለክብርህ ፡ ቆምኩኝ
ጉልበቴን ፡ አድስ ፡ ይሁንልኝ ፡ ኃይል

አዝ፦ ፀጋህ ፡ ይብዛልኝ ፡ ለክብርህ ፡ አቁመኝ
ላገልግልህ ፡ ጉልበቴን ፡ አድስ (፫x)