ጦሬ ፡ የምዋጋበት (Torie Yemewagabet)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ጦሬ ፡ የምዋጋበት
ጋሻዬ ፡ የምመክትበት
ጠላቴን ፡ የማሸንፍበት
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጉልበት

አብሮኝ ፡ አለ ፡ በመከራ
ይሰማኛል ፡ በጭንቀት ፡ ስጣራ
ከሚያስፈራው ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን
ይጠብቀኛል ፡ ጌታ ፡ ልጁን ፡ እኔን

አዝ፦ ጦሬ ፡ የምዋጋበት
ጋሻዬ ፡ የምመክትበት
ጠላቴን ፡ የማሸንፍበት
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጉልበት

ወደ ፡ ጽዮን ፡ ስሄድ ፡ ሳመራ
ዳገቱን ፡ እያየሁኝ ፡ ስፈራ
ያጽናናኛል ፡ ያቆመኛል
ድካም ፡ አጥፍቶ ፡ ኃይል ፡ ይሰጠኛል

አዝ፦ ጦሬ ፡ የምዋጋበት
ጋሻዬ ፡ የምመክትበት
ጠላቴን ፡ የማሸንፍበት
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጉልበት

ልቋቋመው ፡ በማልችለው
ፈተና ፡ ውስጥ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
እጄን ፡ ይዞ ፡ ና ! ይለኛል
እንደማይለቀኝ ፡ ቃል ፡ ገብቶልኛል

አዝ፦ ጦሬ ፡ የምዋጋበት
ጋሻዬ ፡ የምመክትበት
ጠላቴን ፡ የማሸንፍበት
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጉልበት