ጢሰኛ ፡ ስደተኛም ፡ እንዳባቶቼ ፡ ነኝ (Tisegna Sedetegnam Endabatochie Negn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ጢሰኛ ፡ ስደተኛም ፡ እንዳባቶቼ ፡ ነኝ
ቤቴም ፡ በላይ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ በዚህ ፡ በታች ፡ አይገኝ
በላይ ፡ ግን ፡ ቸር ፡ አባቴ ፡ ቤቱን ፡ ከፍቶልኛል
እኔም ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ልኖር ፡ ያስመኘኛል
ግሩም ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ወዲያ ፡ ስመለከት ፡ ይግላል ፡ ደስታዬ

ስለእኔ ፡ ሞትን ፡ ቀምሶ ፡ ከሞትም ፡ ያዳነኝ
ያን ፡ ቸር ፡ ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ በዚያ ፡ ልገናኝ
የደስታ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ በዚህ ፡ ቢኖረኝም
ወዲያ ፡ ግን ፡ ወደርሱ ፡ ናፍቆት ፡ አይለቀኝም
ግሩም ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ወዲያ ፡ ስመለከት ፡ ይግላል ፡ ደስታዬ

በምድር ፡ ኃጢአቴ ፡ ሁሉን ፡ አረከሰ
ውኃ ፡ እንደሚፈሥም ፡ በሁሉ ፡ ደረሰ
ባያስፈርድብኝ ፡ እንኳ ፡ ሰላም ፡ ይነሳኛል
ወዲያ ፡ ግን ፡ ስገባ ፡ ፍፁም ፡ ይለቀኛል
ግሩም ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ወዲያ ፡ ስመለከት ፡ ይግላል ፡ ደስታዬ

ልቆይ ፡ ልታገስ ፡ ገና ፡ አይቀርም ፡ ተስፋዬ
ሊወስደኝ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ይመጣል ፡ ኢየሱስዬ
አሁን ፡ በዕምነት ፡ ብቻ ፡ ያለኝን ፡ ገንዘቤ
ልቀበለው ፡ በምሉ ፡ ስደርስ ፡ ወዳገሬ
ግሩም ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ወዲያ ፡ ስመለከት ፡ ይግላል ፡ ደስታዬ