ጠውልጐ ፡ እንደ ፡ አበባ ፡ ሲቀር (Tewlego Ende Abeba Siqer)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ጸውልጐ ፡ እንደ ፡ አበባ ፡ ሲቀር
የዓለም ፡ ተስፋ
ውኃ ፡ ፈልቆ ፡ በበረሃ
ለተጸማ
ነፍሱን ፡ የሚያረካ

ክርስቶስ ፡ ፍቅሩን ፡ እያሳየን
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ሆነልን
በደሙ ፡ የሚያድነን
ለነፍሣችን
ሃብቱን ፡ አቀረበልን

በዓለም ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ብቻ
ከጭንቀት ፡ የሚረዳ
ሊሰጥ ፡ ለኃጥአን ፡ ይቅርታ
ምሉ ፡ ፀጋ
ኑዛዜ ፡ ለሚገባ

ከኢየሱስ ፡ ነው ፡ ብርሃን ፡ ዕውነት
ሆነልን ፡ መንገድ ፡ ሕይወት
የፈለገው ፡ ያገኘዋል
ይሰጠዋል
ለለመነው ፡ በዕምነት

በመላ ፡ ዕድሜያችን ፡ ቀን
እጆቹን ፡ ዘረጋልን
ገና ፡ እኛን ፡ ይተገሣል
ይጦረናል
ዕምነትን ፡ አጸናልን

በጐ ፡ እረኛ ፡ ሆኖዋል
የጐደለውን ፡ ይመላል
በወንጌል ፡ በቅዱስ ፡ እራት
ሰጠን ፡ ብጽአት
ርህሩህ ፡ ሆኖ ፡ ይኖራል

ከኩነኔ ፡ ሊያድነን
ስንት ፡ ውለታ ፡ ዋለልን
ድል ፡ ይሰጣል ፡ በጦርነት
በቸርነት
ሆነልን ፡ ጤና ፡ ሕይወት

እንደ ፡ አባት ፡ አሳድረን
ፀጋህን ፡ አቅርብልን
ሰላምን ፡ ስጥ ፡ ለችጉር ፡ ነፍስ
ለእኛ ፡ ለግስ
ይህ ፡ ጉዞ ፡ እስኪጨረስ

በሚደርስብን ፡ መከራ
ሆነህልን ፡ ረድዔት ፡ ተስፋ
በጭንቅ ፡ በሞት ፡ አሳልፈህ
በመንግሥትህ
ብጽዕናን ፡ ትሰጣለህ