From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ትውስ ፡ ሲለኝ ፡ የጌታዬ ፡ ፍቅር
ያደረገልኝ ፡ በጐልጐታ
ከአገር ፡ ወደአገር ፡ በመንከራተት
ፀሐይና ፡ ውርጭ ፡ ሲፈራረቅበት
ይሁዳ ፡ ሸጦት ፡ ጴጥሮስ ፡ ሲከዳው
ተከታዮቹም ፡ ጥለውት ፡ ሲሸሹ
የፍጥኝ ፡ ታስሮ ፡ ለፍርድ ፡ ሲነዳ
ጥፊውና ፡ ግርፉ ፡ ሲወርድበት
አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያ ፡ መድህኔ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለእኔ
ትውስ ፡ ይለኛል ፡ የመስቀል ፡ ፍቅሩ
ያደረገልኝ ፡ ውለታ ፡ ሁሉ
አልራሩለትም ፡ አስረው ፡ ሲገርፉት
ያን ፡ መልክ ፡ መልካም ፡ ሩህሩህ ፡ ፈጣሪ
የማይችለውን ፡ መስቀል ፡ አስይዘው
መድህናቸውን ፡ ለፍርድ ፡ ሲወስዱት
ሲጮህ ፡ ሲያነባ ፡ በጣር ፡ ተከቦ
በደም ፡ ላይ ፡ ባሕር ፡ ሆኖ ፡ ሲያነባ
ሲወድቅ ፡ ሲነሳ ፡ አባ ፡ አባት ፡ ሲል
ተሰቃየልኝ ፡ ነፍሱ ፡ እስክትዝል
አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያ ፡ መድህኔ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለእኔ
ትውስ ፡ ይለኛል ፡ የመስቀል ፡ ፍቅሩ
ያደረገልኝ ፡ ውለታ ፡ ሁሉ
ይረሳኛል ፡ ወይ ፡ ያ ፡ የጣር ፡ ጊዜ
መድሃኒቴን ፡ የተሳለቁበት
ከመስቀል ፡ ቅረድ ፡ ራሽን ፡ አድን
እያሉ ፡ ጠላቶቹ ፡ ሲያሾፉበት
ጨለማ ፡ ውጦን ፡ የነበረውን
እኛን ፡ ለማዳን ፡ ከክብሩ ፡ ወርዶ
የዓለምን ፡ ኃጢአት ፡ ያስወገደውን
ታላቁን ፡ መድህን ፡ ነፍሴ ፡ አትረሳውም
አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያ ፡ መድህኔ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለእኔ
ትውስ ፡ ይለኛል ፡ የመስቀል ፡ ፍቅሩ
ያደረገልኝ ፡ ውለታ ፡ ሁሉ
|