ተስፋ ፡ የሰጠኝ ፡ ሕይወትም (Tesfa Yesetegn Hiywotim)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ተስፋ ፡ የሰጠኝ ፡ ሕይወትም
አንድ ፡ ሥም ፡ ተገለጠ
ከምድር ፡ ከሰማያትም
ያ ፡ ድንቅ ፡ ሥም ፡ በለጠ

ያ ፡ ቅዱስ ፡ ሥም ፡ ነው ፡ አምባዬ
ዕርዴም ፡ በጭንቀቴ
በሃዘንም ፡ ነው ፡ ደስታዬ
በችግርም ፡ ሃብቴ

ያ ፡ ሥም ፡ ስለ ፡ አንድ ፡ ርኅሩኅ ፡ ወዳጅ
ይተርክልኛል
ወዳጄም ፡ የሰማይን ፡ ደጅ
ለእኔ ፡ ከፍቶልኛል

አባቴም ፡ እንዲቀበለኝ
ያ ፡ ሥም ፡ ያስታውቃል
አንድ ፡ ብጹዕ ፡ ወደብ ፡ እንዲገኝ
ያ ፡ ቅዱስ ፡ ሥም ፡ ይላል

ስለሚረዳኝ ፡ ምሕረት
ያ ፡ ሥም ፡ ይናገራል
ስጨነቅ ፡ ኃይልና ፡ ረድዔት
ወትሮ ፡ ይሰጠኛል

እንደኔም ፡ የተፈተነ
የሚራራልኝም
መድኅን ፡ እንደተሰጠነ
ይተርካል ፡ ያ ፡ ስም

ያ ፡ ብጹዕ ፡ ስምም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እርሱ ፡ ነው ፡ ተስፋዬ
ዕረፍቴና ፡ ሰላሜ ፡ ነው
በእርሱም ፡ ነው ፡ ደስታዬ

ምድራዊ ፡ አፍ ፡ ያን ፡ ቅዱስ ፡ ስም
ሊያመሰግነው
አይበቃም ፡ እንጂ ፡ በዓርያም
የብጹዓን ፡ መዝሙር ፡ ነው

ግን ፡ ከዚህ ፡ ምድር ፡ በረሃ
ስሄድ ፡ ወደ ፡ አገሬ
ያ ፡ ሥም ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ፍስሐ
ያ ፡ ሥም ፡ ነው ፡ መዝሙሬ

አንድ ፡ ቀንም ፡ ወደ ፡ አገሬ
ኢየሱስ ፡ ሲያደርሰኝ
አዲሱን ፡ መዝሙር ፡ ዘምሬ
ያን ፡ ሥም ፡ ልወድስ ፡ ነኝ