ተራራው ፡ ሸለቆው (Teraraw Sheleqow)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ተራራው ፡ ሸለቆው ፡ ወንዙ ፡ ወንዛ ፡ ወንዙ
ምቹ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጓዙ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጓዙ (፪x)

ጋሬጣው ፡ ለምለም ፡ ሣር ፡ ይሆናል
ሞገዱም ፡ ወጀቡም ፡ ፀጥ ፡ ይላል
ሐሩሩ ፡ መልካም ፡ ጠል ፡ ይሆናል
ጉዞ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ያመቻል

አዝ፦ ተራራው ፡ ሸለቆው ፡ ወንዙ ፡ ወንዛ ፡ ወንዙ
ምቹ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጓዙ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጓዙ (፪x)

ዓለቱ ፡ መልካም ፡ ምንጭ ፡ ይሆናል
አሸዋው ፡ በለስን ፡ ያበቅላል
ጨለማው ፡ ብርሃን ፡ ይሆናል
አንተን ፡ ይዞ ፡ ጉዞ ፡ ያመቻል

አዝ፦ ተራራው ፡ ሸለቆው ፡ ወንዙ ፡ ወንዛ ፡ ወንዙ
ምቹ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጓዙ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጓዙ (፪x)

ነፋሱ ፡ ክብርን ፡ ይሰጣል
መርከቡም ፡ በሰላም ፡ ይጓዛል
ተራራው ፡ ድልድል ፡ ሜዳ ፡ ይሆናል
አንተን ፡ ይዞ ፡ ጉዞ ፡ ይሳካል

አዝ፦ ተራራው ፡ ሸለቆው ፡ ወንዙ ፡ ወንዛ ፡ ወንዙ
ምቹ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጓዙ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጓዙ (፪x)