ተራመድ ፡ በርታ ፡ ጉዞህንም ፡ ቀጥል (Teramed Berta Guzohenem Qettil)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈፅም
ሕይወትህንም ፡ አድን
የመከራ ፡ ጉም ፡ በላይህ ፡ ቢያንዣብብ
አለና ፡ ኢየሱስ ፡ ፍጹም ፡ አታስብ
ቢመስልህ ፡ ጉዞህ ፡ ፍፁም ፡ ተራራ
ደጋፊ ፡ አለህ ፡ ፍጹም ፡ አትፍራ
አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈፅም
ሕይወትህንም ፡ አድን
በኃጢአት ፡ ቁስል ፡ ብትማቅቅም
በሥሙ ፡ ካመንክ ፡ ፍፁም ፡ አትወድቅም
ስለሚመለስ ፡ ጌታ ፡ ከሰማይ
መብራትህ ፡ ይብራ ፡ ለዓለምም ፡ ይታይ
አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈፅም
ሕይወትህንም ፡ አድን
አትሞኝ ፡ ከቶ ፡ በዓለም ፡ ደስታ
ስለማታገኝ ፡ የሕይወት ፡ እርካታ
መቅረዝህ ፡ ይብራ ፡ ቁም ፡ ተዘጋጅተህ
ጌታ ፡ ሲመለስ ፡ ትነጠቃለህ
አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈፅም
ሕይወትህንም ፡ አድን
ቋሚ ፡ ጓደኛ ፡ ስላለህ ፡ ኢየሱስ
በዕምነት ፡ ተጋደል ፡ በተስፋ ፡ ገስግስ
ዓለምን ፡ አትይ ፡ ማብለጭለጯንም
ተስፋ ፡ ከመቁረጥ ፡ አታድንህም
አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ፈፅም
ሕይወትህንም ፡ አድን
|