ትናንት ፡ ከትናንትም ፡ በስቲያ (Tenant Ketenantem Bestiya)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዓለም ፡ መልኳን ፡ ስትቀየር
ስትሾምና ፡ ስትሽር
ኃያላን ፡ ሲሰወሩ
በሞት ፡ ባሕር ፡ ሲቀሩ
ኢየሱስ ፡ አለ ፡ በክብሩ

አዝ፦ ትላንት ፡ ከትላንትም ፡ በስቲያ
ነገም ፡ ከዛም ፡ ለዘለዓለም
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነው
እርሱ ፡ ከቶ ፡ አይለወጥም

አማኝ ፡ ስፍራውን ፡ ሲለቅ
በኃጢአት ፡ ሲጥለቀለቅ
በተቀደሰው ፡ ስፍራ
የጥፋት ፡ ልጅ ፡ ሲያጓራ
የሱስ አለ ሲያበራ

አዝ፦ ትላንት ፡ ከትላንትም ፡ በስቲያ
ነገም ፡ ከዛም ፡ ለዘለዓለም
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነው
እርሱ ፡ ከቶ ፡ አይለወጥም

ምድርን ፡ የበደል ፡ ብዛት
የእሳት ፡ ደን ፡ ሲያለብሳት
ፍጥረት ፡ ሩጫውን ፡ ሲያቆም
ለዘለዓለም ፡ ሲያከትም
 ኢየሱስ አይለወጥም


አዝ፦ ትላንት ፡ ከትላንትም ፡ በስቲያ
ነገም ፡ ከዛም ፡ ለዘለዓለም
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነው
እርሱ ፡ ከቶ ፡ አይለወጥም

የሚወዱት ፡ ሲከዳ
ሕይወት ፡ ሲሆን ፡ ገዳዳ
ነገር ፡ ሲሆን ፡ ተራራ
ሰይጣንም ፡ ሲያቅራራ
ጌታ ፡ ነው ፡ ከእኛ ፡ ጋራ

አዝ፦ ትላንት ፡ ከትላንትም ፡ በስቲያ
ነገም ፡ ከዛም ፡ ለዘለዓለም
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነው
እርሱ ፡ ከቶ ፡ አይለወጥም