ተመስገን ፡ ነው (Temesgen New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ተመስገን ፡ ነው ፡ ተመስገን ፡ ነው
ምን ፡ አለ ፡ ጌታችን?
በአንተ ፡ ያላለፍነው?
በአንተ ፡ ያላሸነፍነው?

ዳገቱን ፡ ወጣነው ፡ አንተ ፡ እየመራኸን
ቁልቁለቱን ፡ ወረድን ፡ አንተን ፡ ተከትለን
ይኸ ፡ ሁሉ ፡ ሲሆን ፡ አንዴም ፡ አልተረታን
በድል ፡ ስላለፍን ፡ እንበልህ ፡ ተመስገን

አዝ፦ ተመስገን ፡ ነው ፡ ተመስገን ፡ ነው
ምን ፡ አለ ፡ ጌታችን?
በአንተ ፡ ያላለፍነው?
በአንተ ፡ ያላሸነፍነው?

አታውቁም ፡ ተባልን ፡ ስምህን ፡ ስለያዝን
እንደ ፡ ሞኝ ፡ ተቆጠርን ፡ በእኛ ፡ ስላለህ
ይሁን ፡ አይከፋንም ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ጌታችን ፡ ስትመጣ ፡ ሁሉም ፡ ይገለጻል

አዝ፦ ተመስገን ፡ ነው ፡ ተመስገን ፡ ነው
ምን ፡ አለ ፡ ጌታችን?
በአንተ ፡ ያላለፍነው?
በአንተ ፡ ያላሸነፍነው?

ነፋስ ፡ ነፈሰበት ፡ በኩራዛችን ፡ ላይ
ለማጥፋት ፡ እንዳይነድ ፡ ለሁሉም ፡ እንዳይታይ
ግን ፡ ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ቦግ ፡ ብሎ ፡ በራ
በርቀት ፡ ያሉትን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እየጠራ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ነው ፡ ተመስገን ፡ ነው
ምን ፡ አለ ፡ ጌታችን?
በአንተ ፡ ያላለፍነው?
በአንተ ፡ ያላሸነፍነው?

የመልካም ፡ ሁሉ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታችን
ቁጣህን ፡ መልሰህ ፡ በፍቅርህ ፡ ያቆምከን
ያ ፡ ሁሉ ፡ ውለታህ ፡ ጌታ ፡ ትዝ ፡ ሲለን
ደግመን ፡ ደጋግመን ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን

አዝ፦ ተመስገን ፡ ነው ፡ ተመስገን ፡ ነው
ምን ፡ አለ ፡ ጌታችን?
በአንተ ፡ ያላለፍነው?
በአንተ ፡ ያላሸነፍነው?