From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ጥላ ፡ ከለላዬ
በምድር ፡ ላይ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ መከታ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ጌታ (፪x)
በሰማያት ፡ ላይ ፡ ለረዴቴ ፡ የሚራመደውን
ረሃቤን ፡ ያጠገበ ፡ እኔን ፡ ያረካውን
ልመናዬን ፡ ከሰማይ ፡ ሰምቶ ፡ ዘንበል ፡ ብሎልኛል
ትላንት ፡ በለቅሶም ፡ ዛሬ ፡ በእርሱ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ብሎኛል
አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ጥላ ፡ ከለላዬ
በምድር ፡ ላይ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ መከታ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ጌታ (፪x)
ከአመታት ፡ በፊት ፡ የገባውን ፡ ኪዳን ፡ ሲፈጽመው
አልተውህም ፡ አልረሳህም ፡ አልጥልህም ፡ ያለው
እኔም ፡ በዚህች ፡ ሕይወቴ ፡ አይሁኝ ፡ ማዳኑን
የሰይጣንን ፡ መንጋጋ ፡ መትቶ ፡ ህዝቡን ፡ መታደጉን
አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ጥላ ፡ ከለላዬ
በምድር ፡ ላይ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ መከታ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ጌታ (፪x)
በጆሮዬ ፡ የሰማሁትን ፡ በዐይኖቼ ፡ አይሁ
እግዚአብሔር ፡ ከመቃብር ፡ በድኑን ፡ ሲጠራው
አለቀለት ፡ አበቃ ፡ ብዬ ፡ አዝኜ ፡ የተውኩትን
ጌታዬ ፡ ነፍስ ፡ ዘርቶበት ፡ ዳግም ፡ ሕያው ፡ ሲሆን
አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ጥላ ፡ ከለላዬ
በምድር ፡ ላይ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ መከታ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ጌታ (፪x)
ለነገዬ ፡ የምለው ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
በምድር ፡ ላለው ፡ ኑሮዬ ፡ ከዚህም ፡ በኋላ
ለነፍሴ ፡ ባለ ፡ አደራ ፡ ዕድሌም ፡ ፈንታዬ
ሌላ ፡ መከታ ፡ የለኝም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ጥላ ፡ ከለላዬ
በምድር ፡ ላይ ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ መከታ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ጌታ (፪x)
|