ተመስገን ፡ ጌታዬ (Temesgen Gietayie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን

በግለት ፡ እንዲቆይ ፡ ሳይደክም ፡ ጉልበቴ
ኃይልህን ፡ አስታጠቅኸኝ ፡ ከላይ ፡ መድሃኒቴ
በብዙ ፡ ውሽንፍር ፡ ቢያጥለቀልቀኝ ፡ ጐርፉ
ጠላቶች ፡ በአንተ ፡ ስም ፡ ሁሉም ፡ ተሸነፉ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን

የኑሮዬ ፡ ተገን ፡ ክብሬ ፡ መከታዬ
ኃይሌም ፡ ይታደሳል ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ተድላዬ
ማዕበሉ ፡ ተነስቶ ፡ ሊያሰጥመኝ ፡ ቢቃጣ
በገሃድ ፡ አያለሁ ፡ ረዳቴ ፡ ስትመጣ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን

የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ አያልቅም ፡ ቢቆጠር
ነነዌም ፡ ብትሰራ ፡ ኃጢአት ፡ በማዘውተር
አምላክም ፡ አስቦ ፡ እነርሱን ፡ ለመምከር
አዘዘው ፡ ዮናስን ፡ ለህዝቡ ፡ እንዲናገር

አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናናነት ፡ ለስምህ ፡ ይሁን