ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ እስከዘለዓለም (Temesgen Eyesus Eskezelealem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለዕውሩ ፡ ብርሃን ፡ ለደካማው ፡ ብርታት
ለበሽተኛ ፡ ፈውስ ፡ ለሙታንም ፡ ሕይወት
ሆነህ ፡ ትገኛለህ ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ተዐምረኛ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ንገሥ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ እስከዘለዓለም (፫x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ የለም (፫x)

ማዕበል ፡ ተነስቶ ፡ እጅግ ፡ ሲያናውጠን
በቃልህ ፡ ገስጸህ ፡ ጸጥ ፡ አደረክልን
ኦ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ልዩ ፡ ነህ
እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ ይክበርልን ፡ ስምህ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ እስከዘለዓለም (፫x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ የለም (፫x)

ከአባት ፡ ከእናት ፡ አንተ ፡ ትበልጣለህ
ከወዳጅ ፡ ከወገን ፡ ኢየሱስ ፡ ትሻላለህ
ማን ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንተን ፡ የሚመስልህ
ሁሉም ፡ ከድቶን ፡ ሲሄድ ፡ ቀሪያችን ፡ አንተ ፡ ነህ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ እስከዘለዓለም (፫x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ የለም (፫x)

የሰላም ፡ ሁሉ ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ
የተጠማችን ፡ ነፍስ ፡ ፍፁም ፡ ታረካለህ
እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ የሆነው ፡ ይህ ፡ ስምህ
በተጠራ ፡ ጊዜ ፡ ይወርዳል ፡ ሰላምህ

አዝ፦ ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ እስከዘለዓለም (፫x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ የለም (፫x)