ተመስገን ፡ ኢየሱስ (Temesgen Eyesus)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ውዳሴ ፡ ይቅረብልህ ፡ ተመስገን
ክብርን ፡ የሰጠኸን ፡ ተመስገን
ከፍ ፡ ከፍ ፡ በልልን ፡ ተመስገን
አንተ ፡ ብቻ ፡ ክብር ፡ ተመስገን

አዝ፦ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጌታ
የሁላችን ፡ ባለውለታ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ስጦታችን
የምንሰጥህ ፡ ከልባችን (፪x)

አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ ፡ ተመስገን
ያለን ፡ የነበርክ ፡ ተመስገን
ዙፋንህ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ተመስገን
እስከ ፡ ፍጻሜው ፡ ተመስገን

አዝ፦ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጌታ
የሁላችን ፡ ባለውለታ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ስጦታችን
የምንሰጥህ ፡ ከልባችን (፪x)

ፍቅርህን ፡ ገልጸሃል ፡ ተመስገን
በቀራኒዮ ፡ መስቀል ፡ ተመስገን
ራስህን ፡ በማዋረድ ፡ ተመስገን
ከክብርህ ፡ ወርደሃል ፡ ተመስገን

አዝ፦ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጌታ
የሁላችን ፡ ባለውለታ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ስጦታችን
የምንሰጥህ ፡ ከልባችን (፪x)

ተቢብ ፡ አዋቂ ፡ ነህ ፡ ተመስገን
ለህዝብህ ፡ ፈርደሃል ፡ ተመስገን
ምስኪኑን ፡ ከጉድፍ ፡ ተመስገን
ከአመድ ፡ አንስተሃል ፡ ተመስገን

አዝ፦ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጌታ
የሁላችን ፡ ባለውለታ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ስጦታችን
የምንሰጥህ ፡ ከልባችን (፪x)

ትጉ ፡ ጠባቂ ፡ ነህ ፡ ተመስገን
እንዳንሰናከል ፡ ተመስገን
በቅን ፡ መርተኸናል ፡ ተመስገን
ወደ ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ ተመስገን

አዝ፦ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጌታ
የሁላችን ፡ ባለውለታ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ስጦታችን
የምንሰጥህ ፡ ከልባችን (፪x)

ገናና ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ፡ ተመስገን
ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ተመስገን
ዛላለም ፡ ብሩክ ፡ ነህ ፡ ተመስገን
ዕድል ፡ ፈንታችን ፡ ነህ ፡ ተመስገን

አዝ፦ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጌታ
የሁላችን ፡ ባለውለታ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ስጦታችን
የምንሰጥህ ፡ ከልባችን (፪x)

አንተ ፡ ደስታችን ፡ ነህ ፡ ተመስገን
ኃይላችን ፡ ሆነሃል ፡ ተመስገን
ሃሴት ፡ ሞልተኸናል ፡ ተመስገን
እስቲ ፡ እናመስግንህ ፡ ተመስገን

አዝ፦ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጌታ
የሁላችን ፡ ባለውለታ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ስጦታችን
የምንሰጥህ ፡ ከልባችን (፪x)

ተስፋችን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ተመስገን
የማታሳፍረን ፡ ተምስገን
ትምክህት ፡ የለን ፡ ሌላ ፡ ተምስገን
አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኛ

አዝ፦ አንተ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጌታ
የሁላችን ፡ ባለውለታ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ስጦታችን
የምንሰጥህ ፡ ከልባችን (፪x)