ተመስገን ፡ ብዬ ፡ አልጠግብም (Temesgen Beyie Altegbem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ውለታው ፡ በዝቶ ፡ የምለው ፡ ጠፋኝ
ያልጠበቅኩትን ፡ ታላቅ ፡ ድል ፡ ሳገኝ
ጌታ ፡ ለነፍሴ ፡ ሰላም ፡ ሆኗታል
ሕይወቴን ፡ ብሰጠው ፡ እንኳን ፡ ኦ ፡ ያንስበታል
ስሙ ፡ ይክበር ፡ ይመስገንልኝ ፡ አሜን ፡ ይመስገን

አዝ፦ ተመስገን ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አልጠግብም
ጌታ ፡ ያደረገውን ፡ ሳየው ፡ ሳስበው ፡ ላሰላስል
ልቤን ፡ ይሞላል ፡ ሰላሙ ፡ ክብር ፡ ለስሙ

ያስጐነበሰኝ ፡ ቀንበር ፡ ተሰብሯል
ቀና ፡ ብያለሁ ፡ መንገዴም ፡ አምሯል
እንዳልራመድ ፡ እግሬን ፡ ያሰረው
የሰይጣን ፡ ወጥመድ ፡ ተሰባበረ
ተፈትቼ ፡ ልራመድ ፡ በቃሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

አዝ፦ ተመስገን ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አልጠግብም
ጌታ ፡ ያደረገውን ፡ ሳየው ፡ ሳስበው ፡ ላሰላስል
ልቤን ፡ ይሞላል ፡ ሰላሙ ፡ ክብር ፡ ለስሙ

ከሳሼን ፡ ረቶ ፡ ደስ ፡ አሰኘኝ
መሸማቀቄን ፡ አስቀረልኝ
ያደፈ ፡ ልብሴን ፡ አወለቀልኝ
ይኸው ፡ አዲስ ፡ ልብስ ፡ አጠለቀልኝ
ከራስ ፡ ጸጉሬ ፡ እስከ ፡ እግር ፡ ጥፍሬ ፡ ነጻሁ ፡ ይመስገን

አዝ፦ ተመስገን ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አልጠግብም
ጌታ ፡ ያደረገውን ፡ ሳየው ፡ ሳስበው ፡ ላሰላስል
ልቤን ፡ ይሞላል ፡ ሰላሙ ፡ ክብር ፡ ለስሙ

ጠላት ፡ ሲፎክር ፡ ተስፋዬን ፡ ቆረጥኩ
እጄን ፡ ሰብስቤ ፡ በሃዘን ፡ ተቀመጥኩ
ያን ፡ ጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ ተንቀሳቀሰ
የሰይጣን ፡ ምሽግ ፡ ተደረመሰ
በጌታ ፡ ስም ፡ ድል ፡ ተቀናጀሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

አዝ፦ ተመስገን ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አልጠግብም
ጌታ ፡ ያደረገውን ፡ ሳየው ፡ ሳስበው ፡ ላሰላስል
ልቤን ፡ ይሞላል ፡ ሰላሙ ፡ ክብር ፡ ለስሙ