ተመሥገን (Temesgen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሁሉን ፡ የፈጠረ ፡ አምላክ ፡ ይመስገን
ዓለምን ፡ ወዶ ፡ ልጁን ፡ እስኪሰጠን
ከሃጢአት ፡ ሊያነፃን ፡ ሕይወቱን ፡ ሰጠን
የሕይወት ፡ መንገድ ፡ ደግሞ ፡ ከፈተልን

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ተመሥገን
ምድር ፡ ሁሉ ፡ ስሙት ፡ተመስገን
ተመሥገን ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይደሰት
በልጁ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ አብ ፡ እንድረስ
ሁሉን ፡ ለፈጠረ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረስ

ኦ ፡ ፍፁም ፡ ደህንነት ፡ በደም ፡ የገዛን
ለአማኙ ፡ ሁሉ ፡ ተስፋ ፡ የሰጠን
የበደለ ፡ ሁሉ ፡ በእውነት ፡ ቢያምን
በዚያችው ፡ ሰዓት ፡ ያገኛል ፡ ይቅርታ

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ተመሥገን
ምድር ፡ ሁሉ ፡ ስሙት ፡ተመስገን
ተመሥገን ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይደሰት
በልጁ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ አብ ፡ እንድረስ
ሁሉን ፡ ለፈጠረ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረስ

እርሱ ፡ አስተማረን ፡ እርሱ ፡ ፈጠረን
በልጁ ፡ በኢየሱስ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አለን
ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ እንነጻለን
ኢየሱስ ፡ እያየን ፡ እንገዛለን

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ተመሥገን
ምድር ፡ ሁሉ ፡ ስሙት ፡ተመስገን
ተመሥገን ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይደሰት
በልጁ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ አብ ፡ እንድረስ
ሁሉን ፡ ለፈጠረ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረስ